ለእንግሊዘኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሃገራት Anglo phone African Countries ፊፋ ያዘጋጀው  ወርክሾፕ ከሚያዝያ 20 – ሚያዝያ 25 2011 ዓ.ም  በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ አስተናጋጅነት ተከናወነ ፡፡

በፊፋ አዘጋጅነት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር እያሱ መርሃፅድቅ እና የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌደሬሽን የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስትራክተር መኰንን ኩሩ ተሳትፈዋል፡፡  

በየብሔራዊ ፌደሬሽኖች (Member Association) ያሉ የቴክኒክ ዳይሬክተሮች ከብሔራዊ ፌደሬሽኖች ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚያከናውኗቸው የእግር ኳስ የልማት ተግባራት ላይ ምንና እንዴት መስራት እንዳለባቸውና ከፕሬዚዳንቱና ከቴክኒክ ኮሚቴው ጋር እንዴት መስራት እንደሚገባ በሚሉ ርእሶች ላይ የተሰጠው ስልጠና በእግር ኳሱ ዙሪያ የተቀላጠፈ ስራ ለማከናወንና በቴክኒክና አስተዳደራዊ የአፈፃፀም ዘርፎች ዘመናዊ አሰራርና በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆን እንዳለባቸው ትኩረት የተሰጠበት በ11 የተለያዩ የስልጠና ርእሶች ላይ ትኩረት ተደርጎባቸዋል ፡፡

  1. የፊፋ የእግር ኳስ ልማት አስትራቴጂ በአቅም ግንባታ ዙሪያ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሚና ጐልቶ እንዲታይ በቅድሚያ የቴክኒክ ዳይሬክተሩን የማስፈፀም አቅም ማጐልበት መቻል እንዳለበት ያመላከተ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
  2. በብሔራዊ የእግር ኳስ ፍልስፍና ስልጠናዎች በተግባር በቡድን ስራ ተከናውነዋል፡፡
  3. የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ሚና ምን መሆንና ምን መምሰል እንዳለበት ግልጽ በሆነ የውይይትና የቡድን ስራ ይፋ ወጥቷል፡፡
  4. ብሔራዊ ፌደሬሽኑ ከሌሎች የውጪ ባለድርሻና የውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር ሊኖረው የሚገባው ግንኙነት ተመልክቷል፡፡
  5. የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ከተመራጭ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በተለይም ከፕሬዝዳንቱ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት ተመላክቷል፡፡
  6. በማኔጅመንት ዙሪያ What is Management? በሚል አርዕስት ስልጠና ተሰጥቶበታል፡፡
  7. የቴክኒካል ዲፓርትመንት አደረጃጀት (Set up) ምን መምሰል እንዳለበት የሙከራ ስራ (የቡድን ስራ) ተከናውኗል፡፡
  8. በዚህ አቅራቦት (Presentation) የቴክኒክ ዳይሬክተሩና የጽ/ቤት ኃላፊው የጋራ ኃላፊነት

 የሠራተኞች አቀጣጠርና የስልጠናዎች አፈፃፀም (on Job training) ሃብት ዝግጅት ዙሪያ ሊኖሩ የሚገባቸው የአፈፃፀም ስልቶች በፋይናንስ ዕቅድ ዝግጅትና በጀት አዘገጃጀት ምን መምሰል እንዳለበትና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ በስፋት የውይይትና የተግባር ልምምዶች (Model approaches) ተከናውነዋል፡፡

ከስልጠናው መጠነ-ሰፊ ዕውቀትና ልምድ የተቀሰመበት ሲሆን ከዚህ ስልጠና ፌዴሬሽናችን በአሠራር ዙሪያ የተከሰቱ መዘበራረቆች የጠሩበትና አንዱ ብቻውን ያለ ሌላው ምንም ማድረግ እንማይችል አውቆ በቅንጅት የመስራት ልምድና ዕውቀት የተገኘበት ነው፡፡ ከዚህ ስልጠና በመነሳት በመዋቀርና በአሠራር ዙሪያ የተፈጠሩ ክፍተቶችን የማጥበብና የማስወገድ ስራዎች በቅንጅት የሚከናወኑበት ሁኔታ ይፈጠራል ተብሎ ይታሰባል ሲሉ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌደሬሽን የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስትራክተር መኰንን ኩሩ ገልፀውልናል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር እያሱ መርሃጽድቅ በበኩላቸው  በዚህ ስልጠና የዋና ጸሀፊ እና የቴክኒክ ዳይሬክተር ሚና ምን እንደሆነ፤ በአንድነት እና በተናጥል የሚሰሯቸው ስራዎች በዝርዝር መቅረባቸውን አንዲሁም ሌሎች የፊፋ አባል ሀገራት የዋና ጸሀፊ የዕለት ተዕለት ተግባር ምን እንደሆነ የራሳቸውን ልምድ ማካፈላቸውን እና የቴክኒክ ዲፓርትመንት እና የብሄራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ሚና ምን እንደሆነ በስልጠናው ላይ ማብራሪያ መቅረቡን ገልጸውልናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here