ሚያዚያ 25/2011ዓ.ም አዲስ አበባ ፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በየአራት አመቱ በሚደረግ የጠቅላላ ጉባዔ ምርጫ ፌዴሬሽኑን የሚመሩ አካላት ይመረጣሉ፡፡ በምርጫው ክለቦች የክልል ፌዴሬሽኖች እና ማህበራት ተሳታፊ በመሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን የሚመሩ አካላትን ይመርጣሉ፡፡ የተመረጡት የስራ አስፈጻሚ አካላት በፌዴሬሽኑ ውስጥ ልዩ ልዩ  ቋሚ ኮሚቴዎችን በበላይነት ያስተዳድራሉ፡፡ እነዚህ ቋሚ ኮሚቴዎችም ሚከተሉት ናቸው የሊግ ኮሚቴ፤ የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ፤ የብሄራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ፤ የብሄራዊ ህክምና ኮሚቴ፤ የማርኬቲንግ ኮሜቴ፤የሴቶች ልማት ኮሚቴ እና የስፖርታዊ ጨዋነት እና ጸጥታ ኮሚቴን በበላይነት ይመራሉ፡፡ እንዲሁም ገለልተኛ እና ተጠሪነታቸው ለጠቅላላ ጉባዔ የሆኑ የፍትህ አካላት (የዲሲፕሊን እና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ ይደራጃሉ፡፡ እነዚህ ቋሚ ኮሚቴዎች የየራሳቸው ተግባር እና ኋላፊነት ያላቸው ሲሆን በአንዱ ተግባር እና ሀላፊነት ሌላው ጣልቃ አይገባም፡፡ ስራ አስፈጻሚ አባላት ከጠቅላላ ጉባኤው የተሰጣቸውን እምነት በአግባቡ ለመወጣት መልካም ሰነ ምግባርን በተከተለ መልኩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በአንዳንድ የክለብ ደጋፊዎች እና አመራሮች በፍጹም ታማኝነት የሚሰሩ የስራ አስፈጻሚ አባላትን በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ ገጾች የማሸማቀቅ ብሎም የማስፈራራት ስራን የያዙ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልን የሚያበረታቱ በክለብ ደጋፊነት የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ደግሞ ቤተሰብ መስረተው ተከብረው የሚኖሩ የስራ አስፈጻሚ አባላትን ሞራል እና ስብዕና የሚነካ አንደሆነ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባላት ሐሙስ ሚያዚያ 24/2011ዓ.ም በተጠራው አስቸኳይ ሰብስባ አጽኖት ሰጥተው ተወያይተውበታል፡፡

የሀገር ሀላፊነትን ተቀብለው እግር ኳስ ፌዴሬሽኑን እያስተዳደሩ የሚገኙት የስራ አስፈጻሚ አባላት ድግሞ የሚገባቸውን አክብሮት እና ድጋፍ ሊሰጣቸው እንደሚገባ እየታወቀ እከሌ እንዲህ ያደረገው እከሌን ለመጥቀም ነው በሚል የራስን ስሜት ብቻ ለመጠበቅ በሚደረግ ራስ ውዳድነት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚዎቻችን ፎቶ በሶሻል ሚዲያ በመለጠፍ ፈጽም ከኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር  ባፈነገጠ መልኩ ለማሸማቀቅ የሚደረገው ተግባር እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ አባላት ያሳዘነ ብሎም ጉዳዩን ወደ ህግ እንዲወስድ ያስገደደ ሆኗል፡፡ በዚህ ተግባር ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን በክለቦች ስም የሚነቀሳቀሱ ብዙሃኑን የክለብ ደጋፊዎች የማይወክሉ ስረዓት አልበኞች ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እያሳሰበ በፍትህ አካላት እየተለዩ የሚገኙትን ሰዎች በህግ የማስጠየቁን ስራ አጠናክሮ አንደሚቀጥል ያሳስባል፡፡

የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል በጨዋታ ሜዳ በተጫዎቾች ፤ በአሰልጣኞች በክለብ ደጋፊዎች በሚታይበት ጊዜ ገለልተኛ የፍትህ አካላት ( የዲሲፕሊን ኮሚቴ)  አስተማሪ እርምጃዎችን በመውስድ ላይ ይገኛሉ፤ አንዲሁም የተወሰነው የዲሲፕሊን ቅጣት ተጋኗል ወይም አንሷል አልያም አይገባኝም ብሎ በዲሲፕሊን የተቀጣው ወገን ሲያስብ ጉዳዩን ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ባቀረበ ጊዜ ጉዳዩ እደገና እንዲታይ እየተደረገም ይገኛል፡፡ ዳኞች እና የጫዋታ ታዛቢዎች በሜዳ ላይ ለሚሰሯቸው ጥፋቶች እና ስህተቶች ዳኞችን እና ታዛቢዎችን የሚመድበው አካል ከኮሚሽነሩ ሪፖርት አና ከዳኛው ሪፖርት ጉዳዩን በማመዛዘን አስተማሪ እርምጃዎችን የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ ፍትህን ብሎም ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስጠበቅ ምንጠቀምባቸውን ቋሚ ኮሚቴዎቻችንን ለማሸማቀቅ ብሎም እየሰሩት ያለውን መልካም ተግባር ጥላሸት ለመቀባት ብሎም ለማስፈራራት የሚደረገውን ተግባር ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ ሊቃወመው እና ሊያወግዘው እንደሚገባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባላት አቋም ሲሆን  ለክለቦቻቸው ተቆርቋሪ መስለው የፍትህ ስርዓቱ እንዲጓደል የሚያደረጉ አካላትን በማጋለጥ የተሻለ ስፖርታዊ ጨዋነት ያለበት የውድድር ጊዜ አንዲኖር ማድረግ አለበት ብለን እናምናለን፡፡ ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲጓደል የሚያደረጉ ተጫዋቾችን፤ የቡድን መሪዎችን፤ አሰልጣኞችን፤ ደጋፊዎችን ጨዋው ደጋፊ በአደባባይ ሊያወግዛቸው ይገባል፡፡ ሚዲያውም ስፖርታዊ ጨዋነት በሁሉም ዘንድ እንዲሰርጽ የጀመረውን መልካም ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባላት

ሚያዚያ 25/2011ዓ.ም

አዲስ አበባ

###

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here