በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ እግር ኳስ ውድድር የጨንቻ ከተማ እና የጐፋ ባሬንቼ እግር ኳስ ክለቦች 1ኛ ዙር ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ የተፈጠረውን ከባድ የዲስኘሊን ጥፋት በመመርመር የዲስኘሊን ቋሚ ኮሚቴ በጐፋ ባሬንቼ እግር ኳስ ክለብና በተጨዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፋል፡፡ በእዚሁ መሠረት በ90+4 ኛው ደቂቃ ላይ የጨንቻ ከተማ ቡድን ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ የጐፋ ባሬንቼ ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ በፈፀሙት ተመልካቾችን በጣም የሚያስቆጣ ፀያፍ ድርጊት ክለቡ 100 ሺህ ብር እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡ በተጨማሪም ካጠራቀመው ነጥብ ሦስት ነጥብ እንዲቀነስበት፤ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ቀሪ ጨዋታዎችም በ200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝና በፌዴሬሽኑ በተመዘገበ ሜዳ እንዲጫወት መቀጣቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ የጐፋ ባሬንቼ ሦስት ተጫዋቾች የ10 ጨዋታ እገዳና የ10 ሺህ ብር እንዲሁም ሌሎች አራት ተጨዋቾች የ5 ጨዋታ እገዳና አምስት ሺህ ብር እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡ ክለቡ ቀደም ሲል በተካሄደው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ውድድር በፈፀመው የዲስኘሊን ጥሰት በገንዘብና በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወት መቀጣቱ ይታወሳል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here