በ2010 ልክ የዛሬ ዓመት  በዚህ ወቅት ፋሲል ከነማን በመልቀቅ መከላከያ ስፖርት ክለብን በአንድ አመት ውል የተቀላቀለው ዳዊት እስጢፋኖስ በክለቡ ለአንድ ዓመት ያህል መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በትላንትናው ዕለት ከክለቡ ጋር የተጨማሪ አንድ አመት ውል እንደፈረመ ሲነገር የነበረው ዳዊት እስጢፋኖስ በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ውሉን ህጋዊ አድርጓል፡፡ በመሆኑም ከየካቲት 1/2011ዓ.ም እስከ ጥር 30/2012ዓ.ም በሚቆይ የአንድ ዓመት ውል በዛሬው ዕለት ፈርሟል፡፡ በቆይታውም በወር 182,307.79(አንድ መቶ ሰማኒያ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሰባት ብር ከሰባ ዘጠኝ ሳንቲም) ያልተጣራ ደሞዝ ክለቡ የሚከፍለው ይሆናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here