ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ለባህርዳር አለምአቀፍ ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ የሚሆን የ50 ሚሊየን ብር የድጋፍ ቼክ ለአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስረከበ፡፡ ፋብሪካው ለባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ድጋፍ የሚሆን የ አንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍም አበርክቷል፡፡

ቅዳሜ የካቲት 18, 2009 ዓ.ም በባህር ዳር አቫንቲ ብሉ ናይል ሪዞርት ዳሽን ቢራ ፋብሪካ የተዘጋጀውን ቼክ በይፋ አስረክቧል፡፡ በቦታው የተገኙት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉአዳም ጌታሁን ቼኩን ከተረከቡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት ለባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታዲየም እውን መሆን ዳሽን ቢራ ፋብሪካ የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ፋብሪካው ለግንባታ ሂደቱ እንዲውል ያበረከተውን 50,000,000 (ሃምሣ ሚሊዮን) ብር በቅርቡ ለሚጀመረው ለስታዲዮሙ ዘመናዊ መቀመጫ ወንበር እናውለዋለን ብለዋል፡፡

የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ማሩ በበኩላቸው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በሀገራችን ሁለንተናዊ የማህበራዊ ልማቶች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን ባለፉት 16 (አስራ ስድስት) ዓመታት ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ አድርጓል ብለዋል፡፡ በተለይም በስፖርቱ ዘርፍ ትኩረት በማድረግ ክለቦችን በማቋቋም በመደገፍ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ግንባታ በማገዝ እንዲሁም ስፖርታዊ ሁነቶችን ስፖንሰር በማድረግ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል፡፡ እንደ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚው ገለጻ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ይህን በስፖርቱ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም ይበልጥ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ፋብሪካው በዕለቱ ከስቴድዮም ግንባታ ድጋፉ በተጨማሪ ለባህርዳር ከነማ እግር ኳሽ ክለብ የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርከረቷል፡፡ ከዚህ ቀደምም ክለቡ ይበልጥ እንዲጠናከርና የበጀት እጥረት እንዳይገጥመው የ500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር ድጋፍ ከፋብሪካው ተበርክቶለታል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ ከባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ፣ ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር፣ ከባህር ዳር ከተማና ከሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 500 (አምስት መቶ) ያህል ሰዎች ታድመውታል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here