ግንቦት 03/2011ዓ.ም በወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ እና በደደቢት እግር ኳስ ክለብ መካከል ይደረግ የነበረው የ24ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ በጨዋታው ቅድመ ስብሰባ እና በጨዋታው ሰዓት ባለመገኘቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ ምዕራፍ ሶስት አንቀጽ 69 “ሀ” እና “ለ” በተደነገገው መሰረት ለወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ሶስት ነጥብ እና ሶስት ግብ እንዲመዘገብለት ሆኖ ለደደቢት እግር ኳስ ቡድን ዜሮ ነጥብ እና ሶስት ግብ እዳ እንዲመዘገብበት በተጨማሪ የደደቢት እግር ኳስ ቡድን ብር ስልሳ ሺህ (60,000.00) የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል፤ በአንቀጽ 69 ፊደል “ሐ” በተገለጸው መሰረት ለውድድር የቀረበውን ክለብ ወይም ልዩ ልዩ ወጪዎች በሚቀርበው ማስረጃ መሰረት የሚከፍል መሆኑን በዕለቱ ጨዋታ የሜዳ ገቢን በተመለከተ አወዳዳሪውን አካል በጽሁፍ መጠኑን ገልጾ በሚልከው መሰረት እንዲከፍል ይደረግ፤ በአንቀጽ 69 በፊደል “መ” መሰረት የደደቢት እግር ኳስ ክለብ የቡድን መሪ ከማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ለ6ወር እንዲታገዱ ተወስኗል።

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here