የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር የዳኞች እና የታዛቢዎች ግምገማ ትናንት 04/07/2011ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሄደ፡፡ ትላንት በነበረው መድረክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በአንደኛ ዙር ሲመሩ የነበሩ ዳኞች እና የጨዋታ ታዛቢዎች ሙሉ በሙሉ የተሳተፉ ሲሆን ፤ በሁለት ቡድን ተከፍለው ውይይት ያደረጉ ሲሆን ትምህርታዊ ስልጠናዎች ተሰጧቸዋል፡፡

ለዳኞች የስነ ልቦና ስልጠና፤ በጨዋታ የሚሰጥን አድቫንቴጅ በምን መልኩ ማስተናገድ ይቻላል፤  የጨዋታ ሁኔታን መገመት፤ ለጨዋታ የሚደረግ ዝግጅት እንዲሁም በ2011ዓ.ም በአንደኛ ዙር የተፈጠሩ የዳኝነት ስህተቶችን በቪዲዮ ለመማሪያነት በማቅረብ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲቀርቡ ተድርጓል፡፡

ለጨዋታ ታዛቢዎች ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ከነዚህ መካከል ዳኞች በምን መልኩ መመዘን አለባቸው፤ በ2011ዓ.ም በዳኝነት የተፈጠሩ ስህተቶች ለመማሪያነት ቀርበው አስተያየት ተሰጦባቸዋል፡፡ በሁለቱም ቡድኖች በውይይት ሰዓት የተነሱ ጉዳዮች እና ምላሽ የሚያስፈልጉ ጥያቄዎች ከ9፡30 ጀምሮ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ ለኢእፌ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ እና ለጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር እያሱ መርሃ ጽድቅ ቀርበው ምላሽ ተሰቶባቸዋል
ከተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
– የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈጻሚዎች በየ ስታዲየም እየተገኙ ጨዋታዎችን መከታተላቸው መልካም ቢሆንም፤ በሚገኙበት ጊዜ ለጨዋታ ታዛቢዎች መረጃውን እንዲያውቁት ቢደረግ መልካም ነው።
– ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በየክልሉ የሚገኙ የጸጥታ አስከባሪዎች ለክልላቸው ወገንተኛ መሆን ይታያል።
– የዳኞች እና የኮሚሽነሮች ለስራው አስፈላጊ እና የሚመጥነውን አለባበስ መልበስ ይኖርባቸዋል በተለይ ከጨዋታ በፊት ያለው አለባበስ
– አዲሱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እየሰራ ያለው ተግባር የሚያስመሰግነው ነው በዚሁ ይቀጥል።
– አበል በባንክ መሆኑ ጥሩ ቢሆንም ከሰራችሁ በኋላ የሚለው ጉዳይ በደንብ ቢታይ ጥሩ ነው።
-የጨዋታ ስርጭቱ ጥሩ ቢሆንም ግን አሁንም ጥቂት ጨዋታ ብቻ የመራን ስላለን ቢስተካከል፤ ጨዋታ ሲራዘም ወይም ሲቀየር ማካካሻ ጨዋታ ሊሰጠን ይገባል። የሚሰጡት የዲሲፕሊን እርምጃዎች በጣም ጥሩ ናቸው ነገር ግን አሁንም የሚቀሩ ነገሮች አሉ።

– ከጨዋታ በፊት በሚደረገው ስብሰባ ላይ ክለቦች ተሟልተው አይቀርቡም ይህ መስተካከል አለበት።

– ኢንተርናሽናል የወዳጅነት ጨዋታ ስንመራ ለምንድን ነው 900 ብር ሚከፈለው በፊት 300ዶላር ነበር ሚከፈለው ለምን ይህ ሆነ?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በተነሱት ጥያቄዎች ላይ የሚከተሉትን ምላሾች ሰተዋል፡፡  የኢትዮጵያ የእግር ኳስ  ፌዴሬሽን ስራ አሰፈጻሚ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ” በአንድ ጊዜ ለውጥ ምንጠብቅ ከሆነ ከባድ ነው በሂደት ለውጥ ማምጣት እንችላለን። የዳኛ ምደባ ሌላው የተለየ ምደባ እንዲያገኝ አልተደረገም ከአቅም በላይ በሆነ የፖለቲካ ችግር ካልሆነ በቀር፤ ምደባ በብቃት እንጂ በኮታ አይደለም ይህን አናደርግም። ፕሪማች በተመለከተ ከክለቦች ጋር በደንብ ተነጋግረናል። የጨዋታ መላቀቅን ያመጡት አቋማሪ ተቋማት አይደሉም ራሳችንን ማየት ነው ያለብን። ክለቦች የዳኝነት ሂደቱን አድንቀዋል። ያንን ማስቀጠል ነው ያለብን። ወደ ለውጥ ስንገባ ቻሌንጅ ይኖራል።”

የኢትዮጵያ የእግር ኳስ  ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ” ከምስጋና ልጀምር 1ኛ ዙር ላይ የነበረው የዳኝነት ሂደት ጥሩ ነው ግን ሚያኩራራ አይደለም ከነ ክፍተታችን ምስጋናው ይደረሳችሁ። ኮሚሽነሮች ዳኞችን ምትመዝኑበትን መንገድ በደንብ ፈትሹ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስም በመልካምም ሆነ በክፉ የሚነሳው በእናንተ ይሆናል። በድንብ አምብቡ በደንብም ስሩ። Laws of the game ላይ ስልጠና እንስጥላቸው ብለን ከ16ቱ ሁለት ክለቦች ብቻ ናቸው ጠይቀው ስልጠና የተሰጣቸው። ቀና እና ታማኝ ሆናችሁ ህግን ተርጉሙ”

በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በጆሳምቢን ስፖርት ድርጅታቸው አማካኝነት 400ሺህ ብር የሚያወጡ የዳኞች አልባሳትን በስጦታ አስረክበዋል።

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here