የኢትዮጵያ የወንዶች ኘሪሚየር ሊግ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲካሄድ በወጣው መርሃ ግብር መሠረት በክልል ከተማ መጀመሩን አስመልክቶ የመጀመሪያው ጨዋታ በሐዋሳ ከተማ በሲዳማ ቡና እና በፋሲል ከተማ እግር ኳስ ቡድን መካከል ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተካሂዷል፡፡

በእለቱ የነበረው የጨዋታ ሁኔታን በተመለከተ የተመልካቹ ፣ የተወዳዳሪ አካላት እና የአመራሩ ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ እና ስፖርታዊ ጨዋነትን የተላበሰ ሲሆን ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር በመዘመር ጨዋታው የተጀመረ ሲሆን እስኪ ጠናቀቅ ድረስ እግር ኳስ ስፖርቱ በሚፈልገው ስፖርታዊ ስነምግባር በመካሄድ በሲዳማ ቡና 2 ለ 1 አሸናፊነት በሰላም ተጠናቋል፡፡

ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች በአንድነት በጋራ ጨፍረዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም  ለእግር ኳስ ስፖርቱ የበከላቸውን በማድረግ ስፖርታዊ ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ውድድሩ እንዲካሄድ ላደረጉ የስፖርት አፍቃሪው ቤተሰብ፣ ለሁለቱም ክለቦች ለደጋፊዎችና አመራሮች በሙሉ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚካሄዱት ውድድሮች እንደዚሁ በስፖርታዊ ጨዋነት እንደሚካሄዱ ሙሉ እምነቱ ሲሆን መልካም የውድድር ዘመን እንዲሆን ይመኛል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here