የ2009 ዓ.ም የከፍተኛ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡

ነገር ግን በወጣው ኘሮግራም መሰረት ለማከናወን የድሬደዋ ከተማ የአየሩ ፀባይ በአሁኑ ወቅት ሞቃታማ በመሆኑ በተጨዋቾች ላይ ተፅዕኖ እንዳይኖር በማሰብ በ8፡00 ሰዓት ሊደረግ የነበረውን ጨዋታ ኘሮግራም ማሸጋሸግ አስፈልጓል፡፡ በዚሁ መሠረት

 

ተ.ቁ ተጋጣሚዎች ቀን ዕለት ሽልማት  ሰዓት ቦታ
1 መቀሌ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና 11/11/09 ማክሰኞ የደረጃ 10፡00 ድሬደዋ ስታዲየም
2 ወልዋሎ አ/ዩንቨርስቲ ከ ጅማ ከተማ 12/11/09 ረቡዕ የዋንጫ 10፡00 ድሬደዋ ስታዲየም

 

       ከዚህ በላይ በተገለፀው ኘሮግራም መሰረት በቦታው በሰዓቱ ተገኝታችሁ ውድድራችሁን እንድታከናውኑ እያሳሰብን፡-

በዕለቱ ጨዋታ ላይ ተጋጣሚ ቡድኖች በ90 ደቂቃ ጨዋታ ጊዜ ካልተሸናነፋ ለዚህ ውድድር በወጣው የከፍተኛ ሊግ እግር ኳስ ውድድር ደንብ ምዕራፍ 5 በአንቀፅ 2 በተራ ቁጥር 3 መሰረት በ5 /አምስት/ መለያ ምት አሸናፊው ቡድን እንዲለይ የሚደረግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here