የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከታቸው ስማቸው ከሚነሱ ታላላቅ የእግር ኳስ ባለሙያዎች አንዱ የነበሩት የዳኞች የአካል ብቃት /ፊዚካል/ ኢንስትራክተር መብርሃቱ አዲሽ በአደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዚያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል፡፡

የዳኞች የአካል ብቃት ኢንስትራክተር መብርሃቱ አዲሽ በዳኝነት ሙያቸው በዳኞች ኢንስትራክተርነት፣ /በኮሚሽነርነት/ በጨዋታ ታዛቢነት በኢንተርናሽናል ዳኝነትና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ አመራርነት ለበርካታ ዓመታት በእግር ኳስ ስፖርት የበኩላቸውን አስትዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል፡፡ ኢንስትራክተር መብርሃቱ ባለትዳርና የ4 ወንዶች እና የ2 ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ፡፡ የቀብር ስነሥርዓታቸው ሚያዚያ 2 ቀን 2011 ዓ.ም በተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ቤተሰቦቻቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የሚፈፀም ይሆናል፡፡  

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢንስትራክተር መብርሃቱ ሃዲሽ ዜና እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላ የእግር ኳስ ቤተሰቡ መፅናናትን ይመኛል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here