ዳንግላ ከተማ እግር ኳስ ክለብ እና ላስታ ላሊበላ እግር ኳስ ክለብ በቀን 18/06/2011 ዓ.ም በተጫወተው ጨዋታ ላይ በተፈጠረ ፀብ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በደብዳቤ ቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ.አ.9/093 በቀን 26/06/2011 ዓ.ም ዳንግለ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ላይ ውሳኔ መወሰኑ ይታወቃል፡፡በመሆኑም በዚሁ ጉዳይ ላይ ዳንግለ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የይግባኝ አቤቱታ እና በደብዳቤ ቁጥር ዳ/ብ/እ/ክለብ 031/22/2011 በቀን 22/08/2011 ዓ.ም ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ ለፌዴሬሽኑ አቅርቧል፡፡ በዚሁ መሠረት ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ ዲሲፕሊን ኮሚቴው የወሰነው ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ ተብሏል፡፡

ናሽናል ሲሚንቶ እግር ኳስ ክለብ እና ኢትዮጵያ ኮንስትንክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እግር ኳስ ክለብ በቀን 28/07/2011 ዓ.ም በተጫወተው ጨዋታ ላይ በተፈጠረ ፀብ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በደብዳቤ ቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ.አ.9/0286 በቀን 14/08/2011 ዓ.ም ናሽናል ሲሚንቶ እግር ኳስ ክለብ ላይ ውሳኔ መወሰኑ ይታወቃል፡፡በመሆኑም በዚሁ ጉዳይ ላይ ናሽናል ሲሚንቶ እግር ኳስ ክለብ የይግባኝ አቤቱታ እና በደብዳቤ ቁጥር NC/SP0/26/19 በቀን 24/08/2011 ዓ.ም ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ ለፌዴሬሽኑ አቅርቧል፡፡ በዚሁ መሠረት ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ ዲሲፕሊን ኮሚቴው የወሰነው ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ ተገለጸ ፡፡

ዳሞት ከነማ እግር ኳስ ክለብ እና አማራ ፖሊስ እግር ኳስ ክለብ በቀን 22/07/2011 ዓ.ም በተጫወተው ጨዋታ ላይ በተፈጠረ ፀብ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በደብዳቤ ቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ.አ.9/0240 በቀን 07/08/2011 ዓ.ም ዳሞት ከነማ እግር ኳስ ክለብ ላይ ውሳኔ መወሰኑ ይታወቃል፡፡በመሆኑም በዚሁ ጉዳይ ላይ ዳሞት ከነማ እግር ኳስ ክለብ የይግባኝ አቤቱታ በቀን 14/08/2011 ዓ.ም ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ ለፌዴሬሽኑ አቅርቧል፡፡ በዚሁ መሠረት ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ ዲሲፕሊን ኮሚቴው የወሰነው ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ ተባለ ፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here