የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ባደረገው አስኳይ ስብሰባ ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ የቀረበለትን የጨዋታ ይራዘምልኝ ጥያቄን ተመልክቶ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ደደቢት እግር ኳስ ክለብ ለተጫዋቾች ያለፉትን የ3 ወራት ደመወዝ ባለመክፈላችሁና ተጫዋቾቻችሁ ልምምድ በማቆማቸው ምክንያት ቀጣይ ጨዋታ እንዲራዘምላችሁ በቁጥር ደ/ደ/ስፖ707/11 በቀን 09/08/2011 ዓ.ም ለኢት/እ/ፌዴሬሽን በአድራሻ በተፃፈ ደብዳቤ መጠየቃችሁ ይታወሳል፡፡

ስለሆነም የሊግ ኮሚቴ ሚያዚያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ያቀረባችሁትን ጥያቄ ከመረመረ በኋላ ፡-

    1ኛ / ያለፉት 3 ወራቶች ደመወዝ ለተጫዋቾቻችሁ አለመከፈሉ አግባብ ባለመሆኑ

   2ኛ/ ተጫዋቾቻችሁን ወደ ልምምድ የማስገባት ሥልጣን የክለቡ በመሆኑ

  3ኛ/ ምንም አይነት ከክለቡ አቅም በላይ የሆነ አስገዳጅነት በሌለው ሁኔታ የጨዋታ ፕሮግራም ማራዘም ተገቢ ሆኖ ባለመገኘቱ

  4ኛ/ በአጠቃላይ ክለቡ በኢት/እ/ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 5 ምዕራፍ 2 አንቀጽ 79 እና 80 በተጠቀሰው መብትና ግዴታዎች መሠረት መፈፀም ሲገባው በዚህ ዓይነት መልኩ መጠየቁ ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄው ውድቅ ሆኖ ቀደም ሲል በወጣው ፕሮግራም መሠረት ቀጣይ ጨዋታዎቻችሁን እንድታከናውኑ ተወስኗል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ከላይ በተጠቀሰው የዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

በአንዳንድ ሚዲያዎች ጨዋታው ተራዝሟል መባሉ ሀሰት መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያረጋግጣል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here