የክለቦች ፈቃድ አሰጣጥን በተመለከተ ከሚያዚያ 17-18/2011ዓ.ም ከአባል ሀገራት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ለተውጣጡ የክለብ ላይሰንሲግ ሀላፊዎች እና የመጀመሪያ ውሳኔ ሰጪ አካላት ባሉበት በኡጋንዳ ካምፓላ ካፍ የሁለት ቀናት ስልጠና ሰጠ፡፡ በዚህ ስልጠና ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአቶ ተድላ ዳኛቸው የፌዴሬሽኑ የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማኔጀር እና በአቶ እሱባለው አበጀ የመጀመሪያ ውሳኔ ሰጪ አካል ሰብሳቢ ተወክሏል፡፡

የየሀገራቱ የፌዴሬሽን ልኡካን በምድብ 1 እና በምድብ 2 በመክፍል ሁለት የካፍ ክለብ ፈቃድ ኢንስትራክተሮች ባሉበት የፊት ለፊት ውይይት የተደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በምድብ 2 ከናይጄሪያ እና ከጋና በመጡ ኢንስትራክተሮች እና ሚስተር አህመድ ሀራዝ ባሉበት ሰፊ ግምገማ እና ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያደረጋቸውን ስራዎች ሪፖርት እና የ2019/2020 የፌዴሬሽኑ ዕቅድ አክሽን ፕላን አቅርቧል፡፡በሪፖርቱም ለሁለት የአፍሪካ እግር ኳስ የክለብ ውድድር ተሳታፊዎች ፈቃድ እንደተሰጠ እና በውድድሩ ተሳታፊ እንደነበሩ፤በሀገራዊ ፈቃድ ላይ በአሁኑ ወቅት የጥሪ ሂደት መተላለፉን እስከ አሁን ሀገራዊ ፈቃድ እንዳልተሰጠ፤ አዲስ የመጀመሪያ ውሳኔ ሰጪ አካል መቋቋሙን በተለይም የህግ ባለሙያ እና የሂሳብ ባለሙያ ያሉት እንደሆነ እና የይግባኝ ሰሚ አካል ከዚህ በፊት የተቋቋመ እንደነበረ እና በአሁኑ ወቅት ሁሉም የሌሉ መሆናቸው በዚህ መሰረት የፌዴሬሽኑ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በተደራቢ እንዲሰራ ሃሳብ እንዳለ እና ሌሎች ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡

በዚህ መሰረት ከኢንስትራክተሮች እና ከሚስተር አህመድ ሀራዝ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ኢትዮጵያ በክለብ ፈቃድ ጠንክራ መሰራት እንዳለባት በተደጋጋሚ ጊዜ የተነጋገርን ሲሆን አሁንም ብዙ መስራት ይጠበቅባችኋል፤ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እንደገና መደራጀት አለበት እንዲሁም በስትራቴጂ ፕላን ተጠቀሙ ማለትም በመጀመሪያ ፕሪሚየር ሊግ በመቀጠል ከፍተኛ ሊግ በተዋረድ መስራት አለባችሁ ብለዋል፡፡ እንዲሁም እሰከ ሰኔ 23/2011ዓ.ም የሚታይ ስራ እንዲሰራ ሚስተር አህመድ ሀራዝ የካፍ ክለብ ላይሰንሲግ ማኔጀር አጽኖት ሰጠው ተናግረዋል፡፡

በ2012 የውድድር ዘመን 16ቱም የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የህጋዊነት ፈቃድ (ለሀገር ውስጥ መወዳደሪያ) የሚያገለግል የህጋዊነት ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክለብ ላይሰንሲንግ ማኔጄር አቶ ተድላ ዳኛቸው ገልጸውልናል፡፡

ሁሉንም መስፈርት በአንድ ጊዜ ክለቦችን አሟሉ ማለት ክለቦቹን ማፍረስ ሊሆን ስለሚችል አንዳንድ ነገሮችን በስትራቴጂክ ዕቅድ ይዞ ተግባራዊ እንዲያደረጉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለህጋዊነት ፈቃድ አሰጣጥ የሚያግዙ መስፈርቶች ዋና ዋናዎቹ አምስት ሲሆኑ እነዚህም

1. የመወዳደሪያ ቦታ ዝግጅት

2. የወጣቶች ልማት

3. የሰው ሀብት አስተዳደራዊ መዋቅር

4. የፋይናንስ ስርዓት(የገቢ እና የወጪ ስርዓት)

5. ህጋዊነት መስፈርት

በዚህም መሰርት የ16ቱም ክለቦች የፊት ለፊት ግምገማ እስከ ግንቦት 30/2011ዓ.ም ለማጠናቀቅ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የክለብ ፈቃድ ማኔጀሩ አቶ ተድላ ዳኛቸው ገልጸውልናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here