ሐምሌ 03 ቀን 2009 ዓ.ም በ9፡00 ሰዓት ሆሳዕና ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከ ሀላባ ከተማ የከፍተኛ ሊግ የሁለተኛውን ዙር 30ኛ ጨዋታ ባደረጉበት ዕለት ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የሀላባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን አምበል የሆነው ቁጥር 95 ትዕግስቱ አበራ የመታወቂያ ቁጥር 1059 የሆነ ተጨዋች የሀድያ ሆሳዕና ከተማ ተጨዋች የሆነው ቁጥር 17 ሔኖክ አርፍጮ የመታወቂያ ቁጥር 1631 ቀደም ባለው ጨዋታ በቀይ ካርድ ተቀጥቶ ቅጣቱን ሳይጨርስ ለሀድያ ሆሳዕና ከተማ ቡድን መሰለፋ ተገቢ ተጨዋች አይደለም በማለት ክስ መስርቷል፡፡

ክለቡ ይህንኑ ክስ ለማጠናከር በቁጥር ሀ.ከ.አ.ክ-128/09 – በ04/11/2009 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ሲያሳውቅ በተጨማሪ አስራት ሚሻሞ የተባለው ተጨዋች በተለያዩ ጨዋታዎች 5 /አምስት/ ቢጫ አይቶ በ03/11/09 ዓ.ም ከቡድናችን ጋር በተደረገው ጨዋታ ተሰልፎ መጫወቱ ተገቢ አይደለም በማለት አቤቱታ አቅርቧል፡፡

የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ በ05/11/09 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የሀላባ ከተማ ቡድን ያቀረበውን ክስ ሲመረምር

1ኛ. የሀድያ ሆሳዕና ከተማ ቡድን ተጨዋች የሆነው ሄኖክ አርፍጮ ክለቡ በቁጥር 313/08 በ21/10/09 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ይቅርታ እንዲደረግለት ያቀረበውን ጥያቄ ፌዴሬሽኑ ተመልክቶ በቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ/አ – 9/133 በ29/10/09 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ይቅርታ ያደረገለት ስለመሆኑ ለክለቡ እና ለተጨዋቹ ከተፃፈው ደብዳቤ ለማረጋገጥ በመቻሉ በ03/11/09 ሀድያ ሆሳዕና ከሀላባ ከተማ በተደረገው ጨዋታ ለቡድኑ ተሰልፎ መጫወቱ ተገቢ ተጨዋች ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ የዕለቱ ውጤት እንዲፀድቅ ተወስኗል፡፡

2ኛ. ተጨዋች አስራት ሚሻሞን፡- በተመለከተ በ03/11/09 በተደረገው ጨዋታ በተጠቀሰው ጨዋታ ላይ በደንቡ መሰረት ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ክስ ባይቀርብም ስለተጨዋቹ ኮሚቴው የዳኛ ሪፖርት በዝርዝር ባጣራበት ጊዜ

  1. በ16/4/09 ዓ.ም ከአርሲ ነገሌ
  2. በ21/05/09 ዓ.ም ከዲላ ከተማ
  3. በ23/08/09 ዓ.ም ከወልቅጤ ከተማ
  4. በ11/10/09 ዓ.ም ከነቀምት ከተማ የቢጫ ካርድ ማስጠንቀቂያዎች ተመዝግቦ የተገኘ ሲሆን እንደ ሀላባ ከተማ ስፖርት ክለብ አቤቱታ አምስትኛ ቢጫ ያልሞላው ሆኖ በመገኘቱ በዚህ ጉዳይ ላይ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም

3ኛ. ለክስ መመስረቻ ክለቡ ያሲያዘው ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ ለፌዴሬሽኑ ገቢ እንዲሆን በከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ የተወሰነ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

1 አስተያየት

  1. Ye kitat article lay yalut hasaboch yebraru yemote FF 4 cheweta yeteketa techawach meche nw kitatu yeminesaw Halaba kesachuhn le caf fax adergu

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here