የኢትዮጵያ እግር  ኳስ  ፌዴሬሽን ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የ2011 የከፍተኛ እና የአንደኛ ሊግ ውድድር የመጀመሪያ ዙር የዳኞች እና ታዛቢዎች ግምገማ መጋቢት 20/211ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል አካሄደ፡፡ በግምገማው ላይ 230 ዳኞች እና የጨዋታ ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ እና የጽ/ቤት ኃላፊው ዶ/ር እያሱ መርሃጽድቅ በትምህርታዊ ግምገማው የተገኙ ሲሆን ለቀረቡላቸውም ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጠዋል፡፡

 
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ” ዳኞች ሁልጊዜ ብቁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤ ስህተት በማንኛውም ሙያ ይኖራል ነገር ግን ይህ ስህተት ሆን ብሎ የተፈጠረ ነው ወይ የሚለው በደንብ መታየት አለበት፡፡ ሁሉም ሰው የኢትዮጵያን እግር ኳስ ይተቻል ግን ለማስተካከል አስተዋጽኦ ለማድረግ አይሞክርም። በዳኝነቱ በኩል በታቻለ መጠን ካለፊት ጊዜያት አንጻራዊ መሻሻል ይታያል ነገር ግን አሁንም ይቀረናል ብለዋል፡፡ ማሃል ሜዳ ላይ በእጅ የተነካ ኳስ እንደ ፔናሊቲ ሚጮህበት ሀገር ላይ ነው ያለነው። ሰሞኑን በተደረገው የአካል ብቃት ፈተና ያላለፋችሁ ዳኞች ይህ ፍጻሜ አይደለም ራሳችሁን አሻሽላችሁ ለሌላ ፈተና ከ6ሳምንት በኋላ ተዘጋጁ ብለዋል። በተጨማሪም ዳኞች ከዘመኑ የእግር ኳስ ህጎች ጋር ለመሄድ ማንበብ በጣም እንደሚያስፈልጋቸው የገለጹ ሲሆን በአካል ብቃት ብቁ ለመሆን መስራት አለባችሁ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል። አክለውም እዚህ ውስጥ ብዙ ወጣቶች አላችሁ እናንተ ወደ ሌላ የዳኝነት ምዕራፍ  ለማደግ መዘጋጀት አለባችሁ የሚል ምክር ለግሰዋል፡፡  

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ “በሁለት ቀን የዳኞች የአካል ብቃት ፈተና የከፍተኛ ሊግ ውስጥ ያሉ ዳኞች የተሻለ ሰርተው እንደመጡ ተረድተናል ማሳያውም ከተፈተኑት 153 ዳኞች 7ቱ ፈተናውን ማለፍ አልቻሉም። ከ110 ብሄራዊ ሊግ ዳኞች 14ቱ ፈተናውን ማለፍ አልቻሉም። ኮሚሽነሮችንም የማጥራት ስራ እንሰራለን” ብለዋል፡፡ በመቀጠለም ከኮሚሽነሮች እና ዳኞች ጥያቄዎችን ተቀብለዋል፡፡

ከኮሚሽነሮች የቀረቡ ጥያቄዎች


“ክልል ጨዋታዎች ላይ የደህንነት ከለላ አለማግኘት ፖሊሶች ወይም የጸጥታ አካላት የክለብ ደጋፊ መሆን ከለላ አለምስጠት፤ ረጅም አመት በኮሚሸርነት በአንደኛ ሊግ ብንሰራም ወደ ከፍተኛ ሊግ ማደግ አልቻልንም ለምን? የዳኞች እና የታዛቢዎች ኢንሹራንስ ከምን ደረሰ? የተመቱ ዳኞች በራሳቸው ነው እየታከሙ ያሉት ካሳ ቢሰጣቸው መልካም ነው? “

ከዳኞች የቀረቡ ጥያቄዎች


” እንደዚህ አይነት መድረክ በመዘጋጀቱየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክቡር ፕሬዝዳንቱን እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢን እናመሰግናለን። የደህንነት ጉዳይ ትኩረት ቢሰጠው፣ አጥር የሌላቸው የብሄራዊ ሊግ ሜዳዎች መፍትሄ ቢሰጠው፣ የኢንሹራንስ ጉዳይ ከምን ደረሰ? ይህ ስልጠና ሰፊ ጊዜ ቢኖረው መልካም ነው።”

ለተነሱ ጥያቄዎች የሚከተሉት ምላሾች ተሰተዋል

ኢ.እ.ፌ ስራ አስፈጻሚ እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ” ከክፍያ ጋር የተነሱትን እንቀበላለን እናስተካክላለን፤ ማንኛውም ክለብ አንደኛ ሊግ ላይ መክፈል ያለበት ማይከፍል ከሆነ በ2012 አይቀጥልም። እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ክለቦች በትክክል መጠበቅባቸውን ሳይከፍሉ ለዳኞች ተቋሙ እየከፈለ አይቀጥልም። ሪፖርት ማቅረብ ጉዳይ ወደ ዘመናዊነት ምትመጡ ከሆነ ዘመናዊ አሰራሮችን መከተል እንችላለን። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን Facebook like አድርጉት መረጃዎችን በቀላሉ መለዋወጥ ስለምንችል። ትራስፖርት ክፍያ ከምንሄድበት ርቀት አንጻር የሚለውን ጥያቄ ጽ/ቤቱ የሚመለከተው ጉዳይ ነው። የዲሲፕሊን ሪፖርት በአግባቡ ተሞልቶ መላክ አለበት፤ ችግር እየተፈጠረ ሪፖርታቸው ላይ ማያካትቱ ኮሚሽነሮች አሉ በአግባቡ መላክ አለበት ርምጃ ለመውሰድም እንዳንችል ምክንያት ሆነዋል።የዳኝነት እድገት ላይ ዘንድሮ ይህንን እንተገብራለን።የስልጠና ማስረጃ ያላስገባችሁ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች በዚህ 15 ቀን ውስጥ አስገቡ በጊዜው ካላስገባችሁ ምደባ የምናቆም ይሆናል። ሁሉም ዳኞች እና ኮሚሽነሮች ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ እኩል ነው ምናየው።”

ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ” ሌብነት ላይ ምንም ዓይነት ትዕግስት የለንም። ኮሚሽነሮች ምደባ ሊለያይ ይችላል፤ ነገር ግን አንዱ አንድ ሌላው ዘጠኝ የተመደበ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው። ተገቢ ያልሆኑ ሜዳዎች በተመለከተ የተነሳው ትክክል ነው። መጸዳጃ ቤት የሌላቸው መወዳደሪያ ሜዳዎች አሉ ይህንን በቀጣይ እርምጃ መውሰድ አለብን። የፍትህ ዲፓርትመንትን ለማጠናከር ጥረት እያደረግን ነው ማስታወቂያ አውጥተናል። ከአበል ጋር በተያያዘ አቅማቸውን ማዳበር ያልቻሉ ክለቦች አሉ። የጨዋታ ሪፖርት ዘመናዊ በሆነ መልኩ እንድታደርሱ ሶፍትዌር ዴቨሎፕ እያድረግን ነው።አንዳንድ ሜዳዎች ላይ በትልቁ የሚታዩ ጉዳዮችን እንዳለዩ እያደረጉ ሪፖርቶች እየደረሱን ነው ከእንገዲህ አላየሁም የሚል ሪፖርት አይሰራም እኔም መስማት አልፈልግም ፤ ከጤና ጋር የተገናኘ ችግር ካለ መመርመር ማይሻሻል ከሆነ ከሙያው መውጣት ነው ሚያስፈልገው መወሻሸት አያስፈልግም ብለዋል። “


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኋላፊ ዶ/ር እያሱ መርሃጽድቅ ” ከክፍያ ጋር በተያያዘ ያለው መዘግየት ለማስተካከል እየሞከርን ስለሆነ ታገሱን፣ በሶፍትዌር ስራዎችን ለመስራት እየሞከርን ስለሆነ ራሳችሁን በቶሎ ከሲስተሙ ጋር ለመሄድ አዘጋጁ፡፡ የተለያዩ አስፈላጊ መረጃዎችን በዌብሳይታችን ላይ ስለ ምንጭን ከዛ ዳውን ሎድ በማድረግ ተጠቀሙ።”

በፕሮግራሙ ፍጻሜም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ለፕሪሚየር ሊግ ዳኞች በድርጅታቸው ጆሳምቢን ስፖርት ትጥቅ እንደሰጡት ሁሉ ለከፍተኛ እና አንደኛ ሊግ ዳኞች ትጥቅ ሰተዋል። እንዲሁም ለኢንስትራክተሮች ቱታ አብርክተዋል። በአጠቃላይ 400,000 ብር የሚገመት ትጥቅ በድርጅታቸው ጆሳምቢን ስፖርት አማካኝነት በስጦታ አስረክበዋል።

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here