በ2009 ዓ.ም ተሳታፊ ከነበሩት 27 ክለቦች ውስጥ ወደ 75 የሚጠጉ ተጫዋቾችን ለዋናው ቡድኖች ተመዘገቡ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተተኪዎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ታምኖበት ተግባራዊ ባደረጋቸው የከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የኘሪሚየር ሊግ ውድድሮች እድሜ ተገቢነት ችግሮችን በመፍታት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡
በታዳጊና በወጣት የተጀመረው የኘሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቂት ዓመታትን የአስቆጠረ ቢሆንም በ2009 ዓ.ም ተሳታፊ ከነበሩት 27 ክለቦች ውስጥ ወደ 75 የሚጠጉ ተጫዋቾችን ለዋናው ቡድኖች በማስመዝገብ ተተኪዎችን በማፍራት ሂደት ተስፋ ሰጪ
ውጤት ሊመዘገብ ችሏል፡፡

EFF Executive Committee Members and Medical Committee Head Dr. NESREDIN ABDUREHIM HOJELE

በተገቢ እድሜ በሚደረጉ ውድድሮች አማካኝነት ወጣቶችን የእድሉ ተጠቃሚ የማድረጉ ሂደት የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪ የሆነውን ማህበረሰባችንን ፍላጐት ለማርካት፣ የአገራችንን መልካም ገጽታ ለመገንባት፣ ብሔራዊ ቡድናችንን ወክሎ የሚሰለፍ ውጤታማ ተጨዋቾን ለማፍራት እና ለበርካታ ባለሙያዎች የሥራ እድል ለመፍጠር ብሎም ወደ ገቢ ምንጭነት ለመለወጥ የሚያስችል መልካም ተስፋ አሳይቷል፡፡
ይህ መልካም ጅምር ቀጣይ እንዲሆን በ2009 ዓ.ም ከተሳተፉ ክለቦች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ሆቴል የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በማዘጋጀትና ከተሳታፊዎች አስፈላጊውን ግብዓት በማሰባሰብ እንዲሁም የካፍና
የፊፋ መመሪያዎችን በማጠናከር፤ በተጨማሪም በ2010 ለመወዳደር የሚችሉ ተጫዋቾችን ዝርዝር በማሳወቅ ወደፊት በሚካሄዱት ውድድሮች ትኩረት መስጠት ስለሚገባው መክረውበታል፡፡

EFF Medical Committee Secretary Dr. AYALEW TILAHUN BESHAHE

የ2010 የውድድር ዘመን የታዳጊዎች እና ወጣቶች ኘሪሚየር ሊግ ከመጀመሩ አስቀድሞ ለእድሜ ተገቢነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትከረት በመስጠት ቀደም ሲል የተፈጠሩ ችግሮች እንዳይከሰቱ እያንዳንዱ ተሳታፊ ክለብ በእድሜ ተገቢነት ላይ የሚችለውን የቤት ሥራ ሰርቶ መምጣት እንደሚገባው ከፌዴሬሽኑ አመራር አካላትና ሙያተኞች የተሰጠው አስተያየት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
በፌዴሬሽኑ በኩል በቴክኖሎጂ የታገዘ የባር ኮድ /መለያ/ ቁጥር እና የጣት አሻራ የመመዝገብ እንዲሁም ከዓለም አቀፋ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር /ፊፋ/ በተሰጠው ስልጠና መሠረት አዲስ የምዝገባ ስርዓት ስለመዘጋጀቱ ይፋ ተደርጓል፡፡

Ethiopian Football Federation IT/FIFA TMS Manager Mr.Michael Emiru

በእዚህ መሰረት የተጫዋቾችን ሙሉ መረጃ፣ የአካል ብቃት እና የእድሜ ተገቢነት ሙሉ የህክምና ውጤት፣የኮንትራት ውል እና ሌሎች መረጃዎችን በማካተት የመታወቂያ ካርድ በማተም አዲስ የአመዘጋገብ ስርዓት ሥራ ላይ የሚውል ሲሆን፤ በተጨማሪም ውድድሩ በሚካሄድበትም ወቅት ድንገተኛ ክትትል በማድረግ የእድሜ ተገቢነት ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚደረገው ጥሪት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጫ
ተሰጥቷል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here