በእንግሊዝ ሊድስ እና ማንችስተር በርካታ እድሜውን የአሳለፈው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሚን አህመድ ቀደም ሲል በማንቼስተር ሲቲ ክለብ የወደፊቱ ተስፋ የሚጣልበት ተጨዋች በመሆን ለስድስት አመታት ተመዝግቦ የነበረ እና በአሁኑ ሰዓት በእንግሊዙ ማውስሆል እግር ኳስ አካዳሚ እየተጫወተ የሚገኘው አሚን ወደ አዲስ አበባ በማቅናት በቶኪዩ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የኦሎምፒክ የእግር ኳስ ዉድድር በአሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ እየተመራ ዝግጅቱን ከጀመረው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ጋር በ34ኛ ዕጩ ተጨዋቾችነት በመቀላቀል የመጀመሪያ ልምምዱን የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም አድርጓል፡፡

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ በልምምዱ ወቅት እንደገለጹት ተጨዋቹ በራሱ ተነሳሽነት ለአገሩ ለመጫወት መምጣቱ ለሌሎች ተጨዋቾች ጥሩ መነሳሳትን የሚፈጥር ሲሆን ቆይታውን የሚወስነው አሚን በሚያሳየው የጨዋታ ብቃት እንደሚሆን እና ይህንንም በቀጣዮቹ የልምምድ ቀናት ከቡድኑ ጋር በሚያደርግው እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here