በያዝነው የሚያዚያ ወር ይካሄዳል የተባለው የሰላም እና የወዳጅነት የእግር ኳስ ውድድር በይፋ መቅረቱን የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ረቡዕ 09/08/2011ዓ.ም ለፌዴሬሽናችን በጻፈው ደብዳቤ ኣሳውቋል፡፡ ይህ ውድደር በኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አጋጅነት በአራት ሀገራት( ኤርትራ፤ ኢትዮጵያ፤ ጅቡቲ፤ ሶማሊያ) ከ20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ሊካሄድ የታሰበ ነበር፡፡ የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው በውድድሩ የጅቡቲ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደማይሳተፍ መግለጹ እንዲሁም የሶማሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በውድድሩ ስለመሳተፉ ማረጋገጫ መስጠት አለመቻሉ ፤ ውድድሩን ላለማካሄድ የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መወሰኑን አሳውቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለመሳተፍ ላሳየው ዝግጁነት ክብር እንዳላቸው ገልጸው፤ ውድድሩ ባለመካሄዱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ይቅረታ በመጠየቅ እሰከ መጨረሻው ላሳየው ዝግጁነት ፌዴሬሽኑን አመስግኗል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here