የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንተርሚዲየቶች ምዝገባ ከሚያዚያ 1 እስከ ሚያዚያ 30/2011ዓ.ም እንደሚያካሂድ ገለጸ፡፡ ከዚህ ቀደም የተጫዋች ወኪል በመባል ይጠራ የነበረውን ስያሜ ኢንተርሚዲየተር በሚል ፊፋ መቀየሩን እና አባል ሀገራት ይህንን አሰራር ተከትለው እንዲሰሩ አሳውቋል፡፡ በዚህ ስራ ውስጥ ገብቶ መስራት የሚፈልግ ማንኛውም ከፌዴሬሽኑ ውጭ ያለ ግለሰብ ወይም ድርጅት ተጫዋቾችን ወይም ክለብን ወክሎ በመደራረደር በክፍያ ወይም በነጻ መስራት የሚችል መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቲ ኤም ኤስ ክፍል ገልጾልናል፡፡

የኢንትርሚዲየት ምዝገባን ለማካሄድ ኢንሹራንስ፤ከወንጀል ነጻ የፖሊስ ማስረጃ፤ የአንድ ዓመት ኢንተርሚዲየተር የምዝገባ ክፍያ 500 የአሜሪካ ዶላር መክፈል እንደሚያስፈልግም አሳውቀውናል፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here