የኢትዮጵያ ከ23ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ማረፊያውን ሸበሌ ሆቴል በማድረግ 34 ተጫዋቾችን በመያዝ ለማሊ ጨዋታው ልምምድ ከጀመረ 8ኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። ከ34 የቡድኑ አባላት መካከል ሁለት ተጫዋቾች ማለትም ያሬድ ከበደ እና ሀብታሙ ተከስተ ጉዳት ገጥሟቸው የነበረ ሲሆን ዛሬ ከጠዋቱ 12:30 ብሄራዊ ቡድኑ በአዲስ አበባ ስተዲየም ልምምዱን በሰራበት ወቅት ከጉዳቱ ያገገመው ሀብታሙ ተከስተ ቀለል ያለ ልምምድ ሰርቷል።

የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ ናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ላለበት የመጨረሻ ጨዋታ በአዲስ አበባ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።
በነገው ዕለት ረቡዕ 04/0711 እና ቅዳሜ 07/07/2011ዓ.ም ኦሎምፒክ ቡድኑ ከሲሸልስ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም የአቋም መለኪያ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል። የረቡዕ ጨዋታ ከቀኑ 11ሰዓት ፤ የቅዳሜው ደግሞ በ10ሰዓት ይጀምራል፤ ስታዲየም መግቢያ ዋጋው በፕሪሚየር ሊጉ የመግቢያ ዋጋ መሰረት ይሆናል።

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here