የኢትዮጵያ ከ23ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከማሊ አቻው ጋር ላለበት ጨዋታ በሸበሌ ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ ዝግጅት ከጀመረ ከሳምንት በላይ ሆኖታል፡፡ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉት የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ለማሊው ጨዋታ ዝግጅት አንዲረዳቸው ባሳለፍነው እሁድ አዲስ አበባ ከገባው የሲሸልስ ዋናው ቡድን ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማደረግ መስማማታቸው ይታወቃል፡፡ የሲሸልስ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከናይጄሪያ ጋር ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን በአዲስ አበባ እያደረገ ይገኛል፡፡ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ሁለቱ ቡድኖች አድርገው የኢትዮጵያ ከ23ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአቡበከር ነስሮ ጎል አሸንፏል፡፡
የፊታችን ቅዳሜ በ07/07/2011ዓ.ም የኢትዮጵያ ከ23ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በ10ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም 2ኛውን የወዳጅነት ጨዋታ ከሲሸልስ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምንም አይነት የስታዲየም መግቢያ ክፈያ እንደሌለ ያሰውቃል፤ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው የኢትዮጵያ ከ23ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድንን እንድታበረታቱ እንጋብዛለን፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here