የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በፈረንሳይ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ቀጥሏል፡፡ በአሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ እየተመራ ከተለያዩ ክለቦች በተመረጡ 26 ተጨዋቾች ዝግጅቱን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በብሔራዊ ቡድኑ ምክትል አሠልጣኝነት ወ/ሮ ሰርክአዲስ እውነቱ ከጥረት የሴቶች እግር ኳስ ክለብ እና በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ሻለቃ ተረፈ ጉደታ እንዲሁም ወ/ሪት ፍቅርተ ዘርጋው ከኤሌክትሪክ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ የብሔራዊ ቡድኑ ወጌሻ በመሆን ቡድኑን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከኬንያ አቻው ጋር የመጀመሪያ ግጥሚያውን መስከረም 07/2010 ዓ.ም በሃዋሳ ፤ የመልሱን ጨዋታ ደግሞ መስከረም 22/2010 ዓ.ም በናይሮቢ እንደሚያከናውን ለውድድሩ ከወጣው ኘሮግራም ለመረዳት ተችሏል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here