የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን እ.ኤ.አ በ2017 ጋቦን  ለምታስተናግደው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ  ለመሳተፍ የሚያስችለውን ዝግጅት እንዲጀምር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

የማሊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመንግሥት ጣልቃገብነት ምክንያት ከማንኛውም ኢንተርናሽናል ውድድሮች በካፍ በመታገዱ በማጣሪያው ውድድር የመጨረሻ ተጋጣሚ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ የታዳጊዎች ዋንጫ እንዲካፈል ጥሪ ተላልፎለታል፡፡

በማሊ ላይ የተላለፈው የእገዳ ውሳኔ እስከ ሚያዚያ 22 ቀን 2009 ዓ.ም ከአልተነሳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሻምፒዮናው በቀጥታ ተካፋይነቱን ያረጋግጣል፡፡ ብሔራዊ ቡድናችን የተጠናከረ ዝግጅቱን ሚያዚያ 9 ቀን 2009 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

 

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here