የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ጋር በመሆን የግማሽ ቀን ውይይት ከፕሪሚየር ሊግ ዳኞች ጋር በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት አድርገዋል። የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ የሰባት ጨዋታ ዕድሜ ይቀረዋል፤ ይህንንም ተከትሎ ዳኞች ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ ውይይቱ አተኩሯል። ቀሪ 7 ጨዋታዎች የሚወርዱ ቡድኖችን እና የዋንጫ አሸናፊ የሚሆነውን ክለብ ለመለየት እጅግ ወሳኝ እንደምሆናቸው መጠን የሚገባው ጥንቃቄ በዳኞች በኩል እንዲደረግ መልዕክት የተላለፈበት መድረክ ነው።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ” ዳኞች ጥሩ በሰሩ ቁጥር ሚመሰገነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው፤ ስለሆነም የምትመሯቸውን ጨዋታዎች ልዩ ትኩረት በማድረግ እና ትክክለኛ የጨዋታ ሪፖርት በማቅረብ ውጤታማ ስራ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ፤ በቀጣይ ጨዋታዎች ከሀሜት የጸዱ እንዲሆን በቪዲዮ ለማስቀረት ዝግጅታችንን አጠናቀናል። “

በውይይት ዳኞች የደህንነት ከለላ በአግባቡ እንዲደረግላቸው አሳስበዋል፤ከጨዋታ በኋላ አሰልጣኞች በዳኞች ላይ የሚሰጡት ፈር የለቀቀ አስተያየት እና ውንጀላ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በዝምታ እንዳያልፈው የሚል ማሳሰቢያ በዳኞች በኩል የተሰጠ ሲሆን እንዲሁም የሙያው ስነ ምግባር ሚጠይቀውን ተግባር ለመፈጸም ቃል በመግባት ውይይቱን አጠናቀዋል።

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here