ጥር 25 ቀን 2011 ዓ.ም ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከ ነቀምት ከተማ የአንደኛውን ዙር 9ኛ ሳምንት የከፍተኛ ሊግ እግር ኳስ ጨዋታ በተደረገበት ዕለት በሁለተኛው አጋማሽ በ82ኛው ደቂቃ ላይ የነቀምት ከተማ 2 ለ 1 የሚሆንበት ግብ በሚያስቆጥርበት ወቅት የአርባ ምንጭ ክለብ ደጋፊዎች በሁሉም አቅጣጫ ወደ ሜዳ ድንጋይ የወረወሩ መሆኑንና በዚህም ምክንያት ጨዋታው ለ15 ደቂቃ የተቋረጠ መሆኑን፤

በ89ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታውን ሂደት በሚረብሽ ሆኔታ የአርባ ምንጭ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ አቶ መሳይ ተፈሪ የቴክኒክ ክልልን በመልቀቅ ወደ ሜዳ በመግባት የዳኛ ውሳኔ ይቀወም የነበረ መሆኑን፤

ውድድሩ ተጀምሮ ከተጠናቀቀ በኃላ የነቀምት ከተማ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆነው አቶ ቾንቤ ገ/ሕይወት የፀጥታ ሐይሎችን በቃል እና በእጅ ምልክት አፀያፊ ስድብ የተሳደብ በመሆኑ

የነቀምት ከተማ ቡድን ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ የሆነው ኢብሳ አበበ ከፀጥታ ሐይሎች ጋር በፈጠረው ችግር ዳኞች ለ30 ደቂቃ ከስታዲየሙ እንዳይወጡ መታገታቸውን ከጨዋታ አመራሮች የቀረበውን ሪፖርት በመመርመር በማጣራት የሚከተለው ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

 

  1. በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲስኘሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 በአንቀፅ 66 በንዑስ አንቀፅ 3 በፊደል ሀ መሰረት የአርባ ምንጭ ከተማ ቡድን ብር 50.000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
  2. የአርባ ምንጭ ከተማ ቡድን በዲስኘሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 በአንቀፅ 66 በንዑስ አንቀፅ 3 በፊደል ለ እና 1 መሰረት አንድ ጨዋታ ከሜዳው ወጭ ወጥቶ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወት ተወስኗል፡፡
  3. የውድድሩን ሜዳ በተመለከተ የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ እንዲወስን ተመርቶለታል፡፡
  4. በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲስኘሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 64 በንዑስ አንቀፅ 2 በፊደል ለ መሰረት የአርባ ምንጭ ከተማ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አቶ መሳይ ተፈሪ 4/አራት/ ጨዋታ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጀው ውድድር እንዲታገድ እና ብር 5.000 /አምስት ሺህ/ ብር እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
  5. በዲስኘሊን መመሪያ አንቀፅ 64 በንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት የነቀምት ከተማ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አቶ ቾምቤ ገ/ሕይወት 4 /አራት/ ጨዋታ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጀው ውድድር እንዲታገድ እና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
  6. በዲስኘሊን መመሪያ አንቀፅ 66 በንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት የነቀምት ከተማ ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ አሰልጣኝ አቶ ኢብሳ አበበ 3/ሦስት/ ጨዋታ እና ብር 3.000 /ሦስት ሺህ ብር/ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
  7. በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲስኘሊን መመሪያ ክፍል — ምዕራፍ 2 በአንቀጽ 80 በንዑስ አንቀፅ 16 መሰረት የአርባ ምንጭ ከተማ ስፖርት ክለብ ለደጋፊዎቻቸው ስለ ስፖርታዊ ጨዋነትና የስፖረት ሕጐች ግንዛቤ እንዲያገኙ በ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ አስተምረው ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በጽሑፍ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተወስኗል፡፡
  8. የቅጣት ገንዘብ የተጣለባቸው አሰልጣኞችም ሆነ ክለቡ ይህ ውሳኔ ለክለቡ በደረሰው በ7 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለፌዴሬሽኑ ሂሳብ ክፍል ገቢ እንዲያደርጉ ተወስኗል፡፡ በውሳኔው መሰረት ካልከፈለ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲስኘሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 በአንቀፅ 33 በፊደል ሸ መሰረት ክፍያው ለዘገየበት ሁለት በመቶ መቀጮ ጨምሮ እንዲከፍሎ ተወስኗል፡፡

 

                                                                  በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

                                                                  የሕዝብ ግንኙነት  ዳሬክቶሬት

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here