የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የከፍተኛ እና የአንደኛ ሊግ ውድድሮችን ለሚመሩ ዋና እና ረዳት ዳኞች የአካል ብቃት መመዘኛ ፈተና በዛሬው እለት 18/07/2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ  እንዲሁም ምዘናውን የሚያካሂዱት ባለሙያዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡የአካል ብቃት መመዘኛ ፈተናውን 153 ዳኞች የተፈተኑ ሲሆን ሰባት ረዳትና ሁለት ዋና ዳኞች ፈተናውን ማለፍ ሳይችሉ እንደቀሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ  አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ የገለፁልን ሲሆን አያይዘውም እንደዚህ አይነቱ ምዘና የአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በሚያወጣው መስፈርት መሰረት የሚሰጥ ሆኖ የዳኞቻችንን የአካል ብቃት የምናይበትና ባለሙያዎቻችን በስነልቦናም ሆነ በአካል ብቃት ብቁ ሆኖ ውድድሮቻችንን ለመምራት የሚያስችለን እንደሆነ እና ይሄውኸ የአካል ብቃት ምዘና በነገው እለትም ለቀሩት ባለሙያዎች ቀጥሎ እንደሚውል ገልፀውልናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here