አዲስ አበባ መጋቢት 11/2011ዓ.ም ፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር ጋር የብቸኛ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ዛሬ መጋቢት 11/2011ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተፈራረመ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ላለፉት አራት ዓመታት 56ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አጋርነቱን በተግባር ያረጋገጠው ዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዋሊያዎቹ ሲነሱ ዋሊያ ቢራ፤ ዋሊያ ቢራ ሲነሳ ዋሊያዎቹ ይታወሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር ለቀጣዮቹ አራት አመታት የሀምሳ ስድሰት ሚሊዮን ብር ብቸኛ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይህ አዲስ ስምምነት የኢትዮጵያ የወንድ እና የሴት ዋና ብሔራዊ ቡድኖችን ላይ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ በተጨመሪም ከዚህ በፊት ከነበረው ስምምነት በተለየ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቢራ እና ማልት መጠጦች ውጪ ከሌሎች የመጠጥ ተቋማት ጋር የስፖነሰር ሺፕ ስምምነት እንዲፈራረም ስምምነቱ ይፈቅድለታል፡፡

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ”የእኛ እና የዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር የብቸኛ ስፖንሰር ሺፕ ስምምነት በዋናነት የምግብና መጠጥን አስመልክቶ የወጣውን አዋጅ መሰረት አድርጎ ለመስራት እና በተመሳሳይ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ለማስጠበቅ ግዴታ እና መብትን በግልጽ የሚያሳይ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ስምምነት ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህ ስምምነት ከ2019 እስከ 2022 እ.ኤ.አ ለተከታታይ 4ዓመታት የሚቆይ ሲሆን የስፖንሰር ሺፑ ስምምነቱም 56ሚሊዮን ብር ነው፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here