በኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የተስተካከይ ጨዋታ መርሃ ግብር ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ እና በፋሲል ከተማ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የተከናወነውን ጨዋታ ኮሚሽነር በነበሩት በኮሚሽነር ሸረፋ ደሊቾ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ የሁለቱ እህትማማች ከተሞች ውድድር ላይ በተፈፀመ የጨዋታ አመራር ችግር የቅጣት ውሳኔ አስተላፏል፡፡

ኮሚሽነሩ ለውድድሩ ተመድበው ወደ ስፍራው ሲንቀሳቀሱ ከጨዋታ አመራሮች ተለይተው መሄዳቸውንና ቀድመው በውድድር ስፍራ አለመገኘታቸውን፣ ከዳኞች ጋር በቅርበት እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ባለመስራታቸው፣ የዕለቱን የጨዋታ አመራሮች ስለውድድሩ አፈፃፀም ግምገማ ለማድረግ በፍፁም ተገቢ ባልሆነ ቦታ ለግምገማ (ለድህረ ውድድር ስብሰባ) መጥራታቸውን፣ በውድድር ሰዓት ወደ አራተኛ ዳኛ በመቅረብ ለምን ይህን ውሳኔ ይሰጣል በማለት በጨዋታው አካሄድ ላይ ጣልቃ መግባታቸውን ፣ ከውድድር ፍፃሜ በኋላ ጉዳዩ ከማይመለከታቸው ግለሰቦች ጋር የጨዋታውን ፊልም ማየታቸውን በሌላው በኩል ከጨዋታ አመራሮች ጋር የውድድሩን ፊልም በጋራ ለማየት በሚል ከፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በመጀመር በተለያየ ቦታ የጨዋታውን ፊልም ለመክፈትና ለማየት ሞክረው እንዳልተሳካላቸው በመግለፃቸው በተጨማሪም አንድ ጨዋታ (ግጥሚያ) ከተጠናቀቀ በኋላ የውድድር አፈፃፀም ሪፖርት በ24 ሰዓት ለአወዳሪው አካል መቅረብ ሲኖርበት ይህ ሳይፈፀም ቀርቶ (ችግር የተከሰተበት ውድድር መሆኑ እየታወቀ) ውድድሩ ከተጠናቀቀ ከሶስት ቀናት (82 ሰዓታት) በኋላ እንዲቀርብ መደረጉ አግባብ ባለመሆኑ፣ የውድድር አፈፃፀም የተቀረፀበት ፊልም ከተረከቡ በኋላ በተሰጠዎ ኃላፊነት መሰረት በተገቢው መንገድ ለአወዳዳሪው አካል መቅረብ ሲገባቸው ይህን ባለማድረጋቸው እና ለብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ያቀረቡት የጨዋታ ፊልም ጥፋት የተፈፀመበትን ክፍል ብቻ የሚገልፅ ትዕይንት ያለበትን በመሆኑ፣ የውድድር ሪፖርት ከማቅረብዎ በፊት ፊልሙን በተለያዩ አካላት በማሳየታቸውና በማስገምገምገማቸው በዚሁ መንስዔ የጨዋታ አመራሮች ተገቢ ላልሆነ ተቃውሞና የስነ ልቦና ችግር በመዳረጋቸው እንዲሁም ከውድድር ፍፃሜ በኋላ ከጨዋታ አመራሮች ጋር በሚደረግ የድህረ ውድድር ስብሰባ ላይ የውድድር አፈፃፀም ሂደቱን ለመገምገም የማይመለከተው አካል ባለበት መወያየቱ ተገቢ ባለመሆኑና በየትኛውም የውድድር ደንብ ላይ ያልተፈቀደ ተግባር መፈፀማቸውን ለሙያው በሰጡት ምላሽ አረጋግጧል፡፡

ይህንኑ መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የካቲት 11 እና የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ባደረጋቸው መደበኛ ስብሰባዎች ስለውድድር አፈፃፀሙ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ በመንተራስ ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በማየት በተጨማሪም የኢትዮጵ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ2011 ዓ/ም ያወጣውን የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ ከግምት በማስገባት ለወደፊት በሪፖርት አሞላል፣ አላላክና የጨዋታ አመራሮች ድህረ ውድድር ግምገማ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሆኖ በእግር ኳስ ዳኞች ኢንስትራክተሮችና ታዛቢዎች የስነ-ስርዓት እርምጃ ደንብ መሰረት ውድድሩን ከመሩበት ዕለት ጀምሮ ለ3 ወራት ከኮሚሽነርነት ስራ በፅኑ የታገዱ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here