በኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር የአንደኛ ዙር የ5 ሣምንት  ኘሮግራም ወልዲያ ከነማ ከ መቀሌ ከነማ እንዲካሄድ በወጣው ኘሮግራም መሠረት ቢጠበቅም በእለቱ ከውድድሩ በፊት በተቀሰቀሰው ረብሻና ከስፖርታዊ ጨዋነት የወጣ ድርጊት ጨዋታው ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሰዎች ሕይወት መጥፋትና ለንብረት ጉዳት እንዲሁም ለጨዋታው መቋረጥ ምክንያት የሆነውን ፀረ ስፖርታዊ ድርጊት በእጅጉ እያወገዘ፤ በውዱ የሰው ልጅ ሕይወት መጥፋት፣ በተጨማሪም በፀጥታ ኃይሎች፣ በደጋፊዎች በአገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች ላይ በደረሰው ጉዳትና እንግልት በእጅጉ ማዘኑን ይገልፃል፡፡

 

በዕለቱ የደረሰውን የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ጉዳትን በተመለከተ የመንግሥት አካል በማጣራት ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ በማመን ሕይወታቸውን ላጡ የስፖርቱ አፍቃሪዎች በድጋሚ ሃዘኑን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለስፖርቱ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡ በተጨማሪም  ለእግር ኳስ ቤተሰቦችና ለመላው ሕብረተሰብም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተከታታይ መረጃዎች ይሰጣል፡፡

 

ፌዴሬሽኑ በሚያካሄዳቸው ውድድሮች በሙሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ ክለቦች፣ ደጋፊዎች፣ የደጋፊዎች ማኀበራት በአጠቃላይ የእግር ኳስ ቤተሰቦች ለሰፖርታዊ ጨዋነት መከበር ትኩረት እንዲሰጡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጥብቅ እያሳሰበ ለሰላማዊ የስፖርት ውድድር ሁሉም የበኩሉን ግዴታ እንዲወጣ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here