የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2011 ዓ.ም የ1ኛው ዙር ውድድር መርሃ ግብርን መሠረት የአደረገ ምርጥ አስር ተጨዋቾች ምርጫ ኘሮጀክት ከገምጃ የህትመትና ማስታወቂያ ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር ለመሥራት ዝግጅቱን አጠናቀቀ፡፡

ኘሮጀክቱ ከሚያዚያ እስከ ሰኔ/2011 ዓ.ም ድረስ በአጭር የፁሑፍ መልክት ምርጥ 10 ተጫዋቾን ከኘሪሚየር ሊግ ክለቦች የእግር ኳስ አፍቃሪው ማሕበረሰብ የሚመርጥ ይሆናል፡፡ ይህንኑ ለማካሄድ የሚያስችሉትን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከኢትዮጵያ ቴሌሙኒኬሽን የአጭር መልዕክት መላኪያውን ቁጥር እንዲሁም በምርጥ 10 ዕጩነት በምርጫው የሚካተቱ 32 ተጨዋቾችን የመምረጡን ሥራ ከፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ተሠርቶ ተጠናቋል፡፡ ይህው ኘሮጀክት ክለቦች በቀጣይ የሚያካሂዱት ጨዋታዎች ላይ ጥሩ የፋክክር መንፈስ እንደሚፈጥር፣ ሊጉ የተሻለ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ እንዲኖረው እና ለተጫዋቾቹ እና ለክለቦቹ ተጨማሪ የፋይናንስ ገቢ ፣ የእውቅና አቅም ለመፍጠት የሚያግዝ እንደሆነ እና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቃቸው ወደትግበራው ለመግባት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ    የፌዴሬሽኑ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ  ታፈሰ ገልፀውልናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here