የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች  ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር ነገ ሚያዚያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት የወዳጅነት ጨዋታ ያካሂዳል፡፡  

የወጣት ቡድኑን ለማበረታታት እና የስፖርት አፍቃሪው ማህበረሰብ ጨዋታውን እንዲመለከት የስታዲየም መግቢያ በነፃ የተደረገ ሲሆን ክቡር ትሪቡኑ ብቻ የዓመት የስታዲየም መግቢያ ክፍያ ለፈፀሙ፣ ለእንግዶችና ለአመራሮች መስተንግዶ ይሆናል፡፡ በመሆኑም መገናኛ ብዙሃኑም ይህን መረጃ ለእግር ኳስ ስፖርቱ አፍቃሪ ማሕበረሰብ በማድረስ የተለመደ ድጋፋን እንዲያደርግላቸው በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here