አዲስ አበባ የካቲት 22/2011ዓ.ም፤  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በቅዳቸው መሰረት የካቲት 23/2011ዓ.ም ከቀድሞ የብሔራዊ ቡድናችን አሰልጣኞች እንዲሁም በአሁን ሰዓት በፕርሚየር ሊጉ በማሰልጠን ላይ ከሚገኙ አሰልጣኞች ጋር በብሉ እስካይ ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ውይይት ያደርጋሉ፡፡

ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረገው የምክክር እና የተሞክሮ መድረክ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ባለውለታ የሆኑ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኞች ልምዳቸውን የሚያካፍሉብት እንዲሁም በአሁን ሰዓት በየክለቡ የሚያሰለጥኑ የፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኞች ለብሄራዊ ቡድን ግብዓት የሚሆኑ ተጫዋቾችን ማፍራት በሚችሉበት እና ለ ብሄራዊ ቡድን አቅም በሚሆኑበት ዙሪያ ውይይታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

እንዲሁም የብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋቾች ሰኞ ዕለት የካቲት 25/2011ዓ.ም ከኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ጋር በብሉ እስካይ ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ውይይት ያደረጋሉ፡፡ በዚህ ውይይት ላይ አሁን ያለውን ብሄራዊ ቡድን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እና በእነሱ ዘመን የነበረው ብሄራዊ ቡድን ምን ይመስል እንደነበር ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት መድረክ ይሆናል፡፡ ለሁለቱም የውይይት መድረኮች በብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪው ተላልፎ አሰፈላጊው ቅደመ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

###

ለበለጠ መረጃ  : www.theeff.org

Ethiopian Football Federation/facebook.com ይጎብኙ

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here