አዲስ አበባ የካቲት 26/2011ዓ.ም፤የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጋር የምክክር መድረክ የካቲት 25/2011ዓ.ም በብሉ ስካይ ሆቴል አካሄዱ፡፡ በዚህ የውይይት መድረክ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኞች ተሳትፈውበታል፡፡
ውይይቱ የተጀመረው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደረጉ በህይወት የሌሉ ባለውለተኞችን በህሊና ጸሎት በማሰብ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ይህ የውይይት መድረክ ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸው ከቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በርካታ ልምዶች በዚህ መድረክ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ይህ አካል ብሄራዊ ቡድኑን ለማሻሻል ትልቅ አቅም እንደሚኖረው አክለው ገለጸዋል፡፡
ለአሰልጣኞች ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 23/2011ዓ.ም እንደቀረበው ሁሉ ለውይይት እንዲያግዝ ሁለት መነሻ ጽሁፎች እና አንድ ጥናታዊ ጽሀፍ በዚህም ላይ ቀረቧል፡፡ በኢንስትራክተር መኮንን ኩሩ የቀረበው መነሻ ጽሁፍ 21 ነጥቦች የተካተቱበት የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ልማት በምን መልኩ መጓዝ እንዳለበት የሚያሳይ ታዳጊዎች ላይ ምን መደረግ እንዳለበት ከእያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ሚጠበቀውን የዳሰሰ መነሻ ጽሁፍ ነው፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ በነበሩ የእግር ኳስ ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ከየትኛው አካባቢ የተገኙ ናቸው የሚል ጥናት በ2005ዓ.ም ተደርጎ የነበረ ሲሆን የዚህ የጥናት ግኝት ለተሳታፊዎች የጥናቱ ባለቤት በሆኑት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የስፖርት ሰነ ልቦና ባለሙያ ሳሙኤል ስለሺ አማካኝነት ቀርቦ አብዛኛው በወቅቱ ይጫወቱ የነበሩት መነሻቸው ከከተሞች እነደነበረ እንዲሁም በወቅቱ ተጫዋቾችን ረዘም ያለ ጊዜ አለማስፈረም ችግር ውስጥ የከተታቸው እና ረጅም ጊዜ አብረው የቆዩ ተጫዋቾች ለቡድን ስኬት ምን ያህል እንዳገዙ በጥናቱ ግኝት ላይ በደንብ ተብራርቷል፡፡
ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ያቀረቡት የውይይት መነሻ ሀሳብ ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ከአለማቀፍ የእግር ኳስ ማህበር ጥናት ጋር በማያያዝ አቅርበዋል፡፡ የተጫዋቾች ጥራት ደረጃ፤ የአሰልጣኖች ና የስልጠና ደረጃ፤ የክለቦች የጥራት ደረጃ ፤ የኢንተርናሽናል ተጫዋቾች መገኘት፤ የብሄራዊ ቡድን አስተዳደር የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን በጥልቀት በማንሳት አብራርተዋል፡፡ እነዚህ ርእሶች የተሻለ ብሄራዊ ቡድን ለመስራት ወሳኞች ናቸው፡፡ ብሄራዊ ቡድን ጥንካሬው እና ድክመቱ የክለቦቻችን የስራ ውጤት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች በርካታ ሀሳቦችን አንስተዋል ከነዚህ መካከል እንደ ሀገር በእግር ኳሳችን የምንከተለው የአጨዋወት ፍልስፍና ሊኖረን ይገባል፤ በሀገራችን እና በሌሎች ሀገሮች ያለው የስፖርት ሳይንስ እድገት ከፍተኛ የሆነ ልዩነት አለበት ይህንን ለማጥበብ እንደ ሀገር መሰራት አለበት፤ እንደዚህ ዓይነት መድረኮች መመቻቸት አለባቸው እንደ ሀገር ባለውለታ በየጊዜው እየተገናኘን ብሄራዊ ቡድናችንን መተቸት አለብን ይህ ዓይነቱ የቅርርብ መድረክ ባለመኖሩ ከስፖርቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሳንገናኝ ለመተቸት የምንጠቀመው ሬዲዮና ቴሌቭዥን ነበር፡፡
የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች እንደገለጹት በፊት የነበረው መከባበር አሁን ባለው ትውልድ እየቀነሰ መጥቷል፤ ይህ ደግሞ በተጫዋቾች ዝውውር ጉቦ እንዲለመድ ሆኗል፡፡ በፊት ለብሄራዊ ቡድኑ ብዙ ያደረግን ሆነን የሚገባው ክብር ስታዲየም በምንገባበት ሰዓት እየተሰጠን አይደለም፤ ብዙዎች በዚህ ምክንያት ከስታዲየም እንዲሸሹ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠን አይደለም ብሄራዊ ቡድን መጫወታችን እንደ አንድ መስፈርት ተቆጥሮ በቀላሉ ስልጠናውን የምናገኝበት ዕድል መመቻቸት አለበት፡፡ የሚዘጋጁ ጥናታዊ ጽሁፎች እኛንም ያማከሉ ሊሆን ይገባል ምክንያቱም ህመሙን ምናውቀው እኛ ነን ሚል ሃሳብ ተነስቷል ይህ ውይይት የክለብ አመራሮች ቢሳተፉበት ጥሩ ነው ተብሏል ብዙ ችግር በእግር ኳስ ውሰጥ እየተፈጠረ ያለው የእግር ኳስ አስተዳደሩ ላይ ክፍተት ስላለበት እንደሆነ የቀድሞ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጠቁመዋል፡፡


የግብ ጣባቂ ጉዳይ እንደ ሀገር አስገዳጅ ህግ ሊወጣበት እንደሚገባ እና አሰለጣጠኑ ላይ ልዩ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ እና ለአንድ ብሄራዊ ቡድን ጥንካሬ የቡድን ህብረት ወሳኝነት እንደሚኖረው እንዲሁም በዚህ ዙሪያ በትኩረት መሰራት እንደሚያስፈልግ አና ታዳጊዎች ላይ የሚሰሩ አሰልጣኞች በጥሩ ዲሲፕሊን የታነጹ መሆን እንዳለባቸው ተገጧል፡፡
የአሰልጣኝነት ስልጠና በተመለከተ የተነሱትን ሀሳቦች ፌዴሬሽኑ በትኩረት እንደሚያቸው የተገለጸ ሲሆን አንዲሁም የተነሱት ነጥቦች ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን ለመስራት የሚያስችሉ በመሆናቸው ለወደፊትም ተመሳሳይ መድረኮች አንደሚዘጋጁ እና የዚህ ውይይት ግኝት በሰነድ እንደሚዘጋጅ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ቃል ገብተዋል፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here