የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፕሪሚየርሊግ እና የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችን ሊያወያዩ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ የካቲት 23/06/2011ዓ.ም  በፕሪሚየር ሊጉ  በማሰልጠን ላይ ከሚገኙ እንዲሁም ብሄራዊ ቡድኑን በተለያዩ ጊዜያቶች ካሰለጠኑ አሰልጣኞች ውይይት እንደሚያደርጉ ገለጸውልናል

በተጨማሪም በ25/06/2011ዓ.ም ከቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች ጋር ብሄራዊ ቡድኑን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት እነደሚያደረጉ አሳውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here