የአዲስ አበባ ስታዲየም ለበርካታ ዓመታት በብቸኝነት የተለያዩ ውድድሩሮችን በከፍተኛ ጫና ከአቅሙ በላይ እያስተናገደ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ የእድሳቶች እና የማስተካከያ ስራዎች እየተሰሩ ውድድሮችን እያካሄደ ቢገኝም በቅርቡ አገራችን ባስተናገደችው የኢትዮጵያው መከላከያ ከ ካሜሮኑ ያንጋ ስፖርት አካዳሚ ኮንፌዴሬሽን ካኘ ጨዋታ ወቅት የውድድሩ ታዛቢ የሰጡትን ሪፖርት መሠረት በማድረግ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው መልዕክት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚገኙ ውስጣዊ ክፍሎች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ መዘጋጀት እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስታዲየሙ ከኢንተርናሽናል ውድድሮች ታግዷል በሚል የተሳሳተ እና መሠረተ ቢስ የሆነ መረጃ ለሕብረተሰቡ የሚያስተላልፋት ከእውነት የራቀ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ይገልፃል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here