የአንደኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ትግራይ ዋልታ ፖሊስ ጨዋታውን ከደብረብርሃን ከነማ አከናውኖ ሲመለስ ትላንት ጠዋት 3፡30 አካባቢ አፋር ውሥጥ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በደረሰው ድንገተኛ የጥይት ተኩስ 6ተጫዋቾች ላይ ጉዳት ደርሶ የአንዱ ህይወት ማለፉን እና ለተጨማሪ ህክምና በሄሊኮፕተር ወደ ደብረዘይት መጓዛቸውን መግለጻችን ይታወቃል፡፡

የትግራይ ዋልታ ፖሊስ ተጫዋቾችን የያዘችው ሄሌኮፕተር  ዛሬ ጠዋት ከቢሾፍቱ ተነስታ መቐለ በሰላም ደርሳለች፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው ተጫዋቾች መካከል አምስቱ ለተጨማሪ ህክምና ሀይደር ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

በትናንትናው እለት በደረሰበት የጥይት ተኩስ ህይወቱ ያለፈው አማኑኤል ብርሃኑ ስርዓተ ቀብር ቀበሌ 12 በምትገኘው ቅድስት ማሪያም ጉግሳ  ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 7ሰዓት ይፈጸማል፡፡ የ24ዓመት ወጣቱ ወጣት  አማኑኤል ተወልዶ ያደገው መቐለ ቀበሌ 03 አካባቢ ሲሆን፤ ከሶስት አመት በፊት ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ የተመረቀ እና ከእጮኛው ጋር ግንቦት 18 ጋብቻውን ሊፈጽም ቀን የቆረጠ ብዙ ህልም የነበረው እግር ኳስ ተጫዋች ነበር፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአማኑኤል ብርሃኑ ቤተሰቦች እና ለትግራይ ዋልታ ፖሊስ መጽናናትን ይመኛል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መንግስት ይህንን አሳዛኝ ተግባር የፈጸሙትን አካላት ለመያዝ እና ለፍርድ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳስባል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here