የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በቀጣይ አገራችን ለምትካፈለው የኦሎምፒክ ማጣሪያ ውድድር የተጨዋቾች ምልመላ ዝግጅት በዋናው፣ ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች ኘሪሚየር ሊግ እና ሌሎች የሊግ ውድድሮችን ከኮቺንግ ስታፋ ጋር በመከፋፋል በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚካሄዱትን ጨዋታዎች እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ከተካሄዱት የተለያዩ ሊግ ጨዋታዎች መካከል በከፍተኛ ሊግ የኢትዮጵያ መድን ከ ወልቂጤ ከተማ በቃሊቲ መድን ሜዳ የተካሄደውን ጨዋታ የብሔራዊ ቡድኑ ምክትል አሠልጣኞች ቡድን ተከታትሎታል፡፡

በሌላውኛው ኘሮግራም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደውን የጅማ አባጅፋርና የፋሲል ከተማን ጨዋታ ተከታትለዋል፡፡ በእለቱም የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ለአሠልጣኙ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ክለቡ በ2010 ዓ.ም የኘሪሚየር ሊጉ አሸናፊ በመሆን በ2011 ዓ.ም በካፍ በአደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች ወቅት የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ለአደረጉላቸው ሙያዊ ድጋፍ እና መልካም የሆነ የልምድ ልውውጥ ሥራዎች እውቅና ለመስጠት በዚሁ ዕለት የምስክር ወረቀት እና የጅማ ባህላዊ መገለጫ የሆኑ ስጦታዎችን አበርክተውላቸዋል፡፡

አሠልጣኙ እንደገለፁልን በተደረገላቸው አቀባበል ምሥጋናቸውን በማቅረብ የዚህ አይነቱ እንቅስቃሴ አገራችን ኢትዮጵያ ለሚያስፈልጋት የእግር ኳስ እድገት እንዲሁም የእግር ኳስ አፍቃሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥር እና የእግር ኳስ ባለሙያውንም የበለጠ እንዲሰራ የሞራል ስንቅ እንደሚሆነው አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here