በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን /ካፍ/ የተዘጋጀው የሴቶች የካፍ “ሲ” ላይሰንስ ሥልጠና በኦሮሚያ ክልል በአምቦ ከተማ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

ከሴኔ 21 እስከ ሐምሌ 5 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ የሚሰጠው የሴቶች ካፍ “ሲ” ላይሰንስ አሠልጣኞች ሥልጠና በዓይነቱ የመጀመሪያው ሲሆን ከ2 ከተማ መስተዳድር ፣ ከ9 ክልሎች እና ከተለያዩ እግር ኳስ ክለቦች የተውጣጡ 40 የእግር ኳስ አሠልጣኞች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ሥልጠናው የካፍ ኢንስትራክተር በሆኑት በአብርሃም መብራቱ፣ በሠውነት ቢሻው፣ በመስከረም ታደሰ፣ በመሠረት ማኒ እና በሠላማዊት ዘርአይ ይሰጣል፡፡ የሥልጠናው አስተባባሪና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴቶች ዴስክ ባለሙያ አልማዝ ፍሰሃ እንደገለጹት በእግር ኳስ ስፖርት የሴቶች ካፍ “ሲ” ላይሰንስ ሥልጠና መጀመሩ ለስፖርቱ እድገት ጠቃሚነቱ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ለሴቶች እግር ኳስ ተጨዋቾች የተሻለ እና ደረጃው ከፍ ያለ ሥልጠና ለመስጠትም ያስችላል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here