በአውሮኘያኑ አቆጣጠር 2020 በቶኪዮ አስተናጋጅነት ለሚካኤደው የሴቶች ኦሎምፒክ እግር ኳስ ዉድድር የአፍሪካ ዞን የዙሩ ቅድመ ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያ ከ ኡጋንዳ የምትጫዋት ሲሆን መጋቢት 25 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

ጨዋታውን ግብዛዊያኑ ሳሀድ አሊ ሻሂንዳ በዋና ዳኝነት ፣ ሀሰን ሀናዲ በአንደኛ፣ አማድ ሺቢል ጋማላት በሁለተኛ እና ሳሚር ሀመድ ኑራ በአራተኛ ዳኝነት፤ ጁቡቲያዊው አሊ ሙሐመድ አብዶ በጨዋታ አሰሰርነት እንዲሁም ናይጄሪያዊው አዳኦቢ ቺሶም በኮሚሽነርነት የሚመሩት ይሆናል፡፡

የመልስ ጨዋታው ከመጀመሪያው ጨዋታ ሦስት ቀናት በኋላ መጋቢት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኡጋንዳ ካምፖላ በስታርታይምስ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን ይህንንም ጨዋታ በዳኝነት ሩዋንዳዊያኑ ኡሙቶኒ አላይን ፣ ሙራንጋዋ ሳንድሪን፣ ኡሙቴሲ አሊሴ እና ሙካንሳንጋ ሳሊማ ከአንደኛ እስከ አራተኛ እንዲሁም በአሰሰርነት ኒካኒካ ማርታ ማሊያዊ እንዲሁም በጨዋታ ኮሚሽነርነት ከቡሩንዲ ቢታአጉኢ አላይን እንደሚመሩት የአለም አቀፋ እግር ኳስ ማህበር /ፊፋ/ ገልዶልናል፡፡

 

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here