የኢትዮጵያ ሴቶች ኘሪሚየር ሊግ ውድድር በ2011 ዓ.ም በሁለቱ ዲቪዚዮኖች እየተካሄደ የሚገኘው የ1ኛ ዙር ውድድሩን እያጠናቀቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የውድድሩ ግምገማ የካቲት 07 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ይከናወናል፡፡

የሁለተኛው ዙር እና የጥሎ ማለፍ ውድድሮች የካቲት 9 እና 10 ቀን 2011 ዓ.ም የሚጀመሩ ሲሆን የውድድሮቹ ኘሮግራም በቀጣይ የሚገለጽ እንደሆነ እና የተጨዋች ተገቢነት ምዝገባ የሁለተኛው ዙር ውድድር ተጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ብቻ የሚስተናገድ መሆኑን የሊግ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here