የኢትዮጵያ  እና  የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በተለያዩ እግር ኳሳዊ  ጉዳዮች በጋራ እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከዚህ ቀደም የአሰልጣኞች ስልጠና በሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካንነት በርካታ የእግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና መከታተላቸው ይታወሳል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ ካፍ በኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ጨዋታ የመምራት አቅም እምነት እየጣለ መምጣቱ፤ ትልልቅ ውድድሮችን እንዲመሩ ምክንያት ሆኗል፤ ውድድሮችንም በብቃት እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

ይህንን የተገነዘበው  የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚያካሂዳቸው ብሄራዊ ሻንፕዮና ውድድሮች  መጋቢት 3/2011ዓ.ም የሚካሄደውን ጨዋታ ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች  እንዲመሩለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በደብዳቤ የጠየቀ ሲሆን፤ የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ይህንን ውድድር የሚመሩ ዳኞችን እንዲያሳውቅ ፌዴሬሽኑ መጠየቁን አሳውቋል፡፡

 

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here