የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀድሞ ዋና ፀሐፊ በነበሩት አቶ አበባው ከልካይ እልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፡፡

አቶ አበባው ከልካይ በአደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 2  ቀን 2011 ዓ.ም ሕይወታቸው አልፏል ፤ ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ ግንቦት 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በላፍቶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡

አቶ አበባው ከልካይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በርካታ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ የቆዩ ባለሙያ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀድሞ ዋና ጸሃፊ በነበሩት በአቶ አበባው ከልካይ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለእግር ኳስ ቤተሰቦች መፅናናትን ይመኛል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here