የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በስመ ጥሩው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጨዋች በአሠግድ ተስፋዬ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፡፡ አሰግድ ተስፋዬ በመልካም ስነ-ምግባሩና በልዮ ችሎታው የአገራችንን እግር ኳስ አፍቃሪዎች የማረከ፣ ሀገራችንን በክብር ያስጠራና ለወጣት ተጫዋቾች ምሳሌ በመሆን በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱት ጥቂትና ምርጥ የእግር ኳስ ስፖርት ተጨዋቾች መካከል አንዱ እንደመሆኑ በድንገት ስለተለየን ሀዘናችንን መራር ነው፡፡ ህፃናትን በማሰልጠን ለሀገራችን እግር ኳስ ትንሳኤ ሳይታክት በመስራት ላይ እያለ በሞት ስለተለየን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለመላው የአገራችን እግር ኳስ ስፖርት ቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ ፌዴሬሽናችን መፅናናትን ይመኛል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here