ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(FIFA)ሲውዘርላንድ ዙሪክ ከሚገኘው ጽፈት ቤቱ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በትላንትናው ዕለት የካቲት 15/2011ዓ.ም በላከው ድብዳቤ የካቲት 3 እና 4/2011ዓ.ም በአዲስ አበባ ለተደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ ምስጋናውን ግልጾ በጻፈው ደብዳቤ በ32ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ስብሰባ ላይ የተገኙት የአለማቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(FIFA) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የስምምነት ሰነድ የአለማቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(FIFA)፤ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(CAF) እና የአፍሪካ ህብረት በጋራ መፈራረማቸውን ገልጸው በዚህ የየሀገራቱ መሪዎች በተገኙበት የአህጉሪቱ ወሳኝ ስብሰባ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(FIFA) በተገኘበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ላደረጉላቸው ድጋፍ እና እገዛ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የአለማቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(FIFA) የምስራቅ እና መካከለኛው እና የሰሜን አፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት የFIFA ቀጠና የልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ተመርቆ መከፈቱ ትልቅ ተግባር ተግባር ነው ፤ የዚህ ቢሮ በአዲስ አበባ መከፈት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና በሌሎች የFIFA አባል ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያሻሽል ግልጸዋል፡፡
ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እግር ኳስን ከማሳደግ አንጻር በርካታ ሀሳቦችን የተለዋወጡበት እና በአካባቢው በሚገኙ ሀገራት በወጣቶች ላይ ስፖርት እንዲሁም እግር ኳስ ስለሚጫወተው ሚና መወያየታቸውን እና የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(FIFA) ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር አብሮ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚሰራ በደብዳቤው አትቷል፡፡
በስተመጨረሻም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የFIFA የቀጠና ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ እነዲከፈት ላደረጉት አስተዋጽኦ እና ድጋፍ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሚመሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ እና አብረዋቸው ለሚሰሩት በኢትዮጵያ እግር ኳስ የተሻለ እንደሚሰሩ መልካም ምኞታቸውን ግልፀዋል፡፡
ደብዳቤው የተላከው በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(FIFA)ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እና በዋና ጽፈት ቤት ኃላፊ  ፋትማ ሳሞራ ፊርማ የተላከ ደብዳቤ ነው፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here