የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካዲስኮ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከጀርመን ሀገር በመጡ የአጥንት፣ የነርቭ ቀዶ ህክምና፣የጉልበት መገጣጠሚያ የአርትሮስኮፒ እና የተለያዩ ቀዶ ህክምና ታዋቂ በሆኑት በዶ/ር ዲተር ወርነር የስፖርት ህክምና ሴሚናር ሚያዚያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም  በኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዲሚ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል ፡፡

በስልጠናው በርካታ የእግር ኳስ ስፖርቱ ሕክምና ባለሙያዎች የሚሳተፋ ሲሆን ከነዚህም የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ፣ የከፍተኛ ሊግ  ክለቦች የስፖርት ህክምና ኮሚቴ አባላት፣ እና ልዩ ልዩ የስፖርት ሕክምና ባለሙያዎችን የሚካተቱ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የህክምና አሠልጣኞቹ ከጀርመን አገር ወደ ኢትዮጵያ በየሁለት ወሩ የሚመጡ ሲሆን በአሁኑ ኘሮግራማቸ ከሚያዚያ 7-10/2011 ዓ.ም ድረስ በካዲስኮ ሆስፒታል በመገኘት የአርትሬስኮፒ እና የተለያዩ ህክምና አገልግሎትን በመስጠት ቆይታ እንደሚያደርጉ ተገልጾልናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here