ለኤሊት ኢንስትራክተሮች ከመጋቢት 18 እሰከ 25/2011ዓ.ም ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ስልጠና ካፍ በሞሮኮ ራባት ይሰጣል፡፡ በስልጠናው ከ19 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ 26 ኤሊት ኢንስትራክተሮች የሚሳተፉ ሲሆን ከምስራቅ አፍሪካ ዞን ሶስት ኤሊት ኢንስትራክተሮች ተሳታፊ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ከኤርትራ ኢንስትራክተር ዳንኤል ዮሃንስ እና ከታነዛኒያ ኢንስትራክተር ሰንደይ ቡርቶን ካዮኒ በኢንስትራክተር አሰልጣኞች ስልጠና ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ይህንን ዕድል ማግኝት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የገለጹ ሲሆን በቆይታቸውም ከሌሎች ኢንስትራክተሮች  ጋር ልምድ ለመለዋወጥ ምቹ አጋጣሚ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here