በቶኪዮ አስተናጋጅነት በአውሮዊያዊያኑ አቆጣጣር 2020 በሚካሄደው የሴቶች ኦሎምፒክ እግር ኳስ የቅድመ ማጣሪያ የአፍሪካ ዞን የመጀመሪያ ዙር ውድድር ሚያዚያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም  ኮንጐ ከ ታንዛኒያ በኮምኘሌክሲ ኦምኒስፖርትስ ስታዲየም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት የሚያካሂዱትን ጨዋታ ኢትዮጵያዊያኑ ዳኞች የሚመሩት ይሆናል፡፡

በዋና ዳኛነት ፀሐይነሽ አበበ፣  ረዳት ዳኝነት ወጋየሁ ዘውዱ እና ይልፋሸዋ ካሳሁን እንዲሁም  በአራተኛ ዳኝነት አስናቀች ገብሬ ከኢትዮጵያ፣ በዳኞች ገምጋሚነት ሲሼልሳዊ እንዲሁም በኮሚሽነርነት ከሩዋንዳ በተመረጡ የጨዋታ አመራሮች እንዲካሄድ በአለም አቀፋ እግር ኳስ ማህበር /ፊፋ/ ጥሪ ተደረገላቸው፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here