በአዲስ አበባ ስታዲየም የቅዳሜና የእሁድ የኘሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ድጋፍ አሰጣጥ በቩቩዜላ ወይም በጡሩንባ መታጀባቸው በጣሙን እንደረበሻቸው አንዳንድ ደጋፊዎች ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

የጡሩንባው ጩኸት ስሜት የሚረብሽ ከመሆኑ ከቩቩዜላ ይልቅ ድምቀትና ሞገስ ያለው የደጋፊዎች ህብረ ዜማና ጭፈራ በጣሙን የተሻለ ስለመሆኑ ደጋፊዎች አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የደጋፊውን አስተያየት መሠረት አድርጐ በሚያሰባስባቸው ተጨማሪ መረጃዎች በመታገዝ እና ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመነጋገር በጡሩምባ የታጀበ ድጋፍ አሰጣጥን በተመለከተ  እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here