በ2019 በፈረሳይ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች  ዓለም ዋንጫ 27 የእግር ኳስ ዳኞች ከየ አህጉራቱ የእግር ኳስ ማህበራት የተመረጡ ሲሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(CAF) ሰባት ዳኞችን አስመርጧል፡፡ ሶስት ዋና እና አራት ረዳት ዳኞች የተመረጡ ሲሆን ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ኢትዮጵያን ትወክላለች፡፡ ከመጋቢት 19 እስከ 25/2011ዓ.ም በኳታር ዶሃ በሚካሄደው የ2019ኙ የሴቶች የዓለም ዋንጫን በዳኝነት ለሚመሩ ዳኞች በተዘጋጀው ሴሚናር ላይ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ  እንድትካፈል  ዛሬ በ16/06/2011ዓ.ም  በአለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር ጥሪ ተደረገላት፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here