ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ዳዊት አሳምነው ላለፉት 19ዓመታት በእግር ኳስ ዳኝነት ያገለገለ እና በአሁን ስዓትም እየሰራ ይገኛል። ባሳለፍነው ሳምንት በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሚያዚያ 26/2011ዓ.ም በመቐለ ስታዲየም የተካሄደውን የደደቢት እና የፋሲል ከነማ ጨዋታን በማሃል ዳኝነት ተመድቦ አጫውቷል።
በዚህ ጨዋታ ላይ በነበረ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ጨዋታው ለተወሰኑ ጊዜያት መቋረጡ ይታወቃል ይህንንም ተከትሎ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፍትህ አካላት ጉዳዩን እየተመለከቱት ይገኛሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስፖርታዊ ጨዋነት እንዲጠበቅ የተለያዩ የስራዎችን መስራቱ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ጨዋታቸውን በገለልተኛ ሜዳ ያካሂዱ የነበሩት የትግራይ እና የአማራ ክልል ክለቦች በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ስራ እና በክልሎች ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት ክለቦቹ በሜዳቸው ጨዋታ ማድረግ መቻላቸው ይታወቃል፤ ሰሞኑን በደደቢት እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ የተፈጠረው ጉዳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በፍትህ አካላት በኩል እየተከታተለ የገኛል። ሆኖም አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ጸሃፊዎች ችግሩን ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ነገሮች እንዲባባሱ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህንን ጨዋታ በማሃል ዳኝነት የመሩት ኢንተርናሽናል አልቢትር ዳዊት አሳምነው ላይ የጨዋታውን ሪፖርት በአግባቡ እንዳያቀርቡ በኢእፌ በኩል ተጽኖ እንደተደረገባቸው ተደርጎ የሀሰት ዘገባዎች እየተገለጹ ይገኛሉ ይህንን አስመልክቶ ኢንተርናሽናል አልቢትር ዳዊት አሳምነው ለዝግጅት ክፍላችን ቀርበው አስተያየታቸውን ሰጠዋል። ” ኢንተርናሽናል አልቢትር ዳዊት አሳምነው እባላለሁ፤ ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የደደቢት እና የፋሲል ከነማን ጨዋታ እንድመራ ተምድቤ ጨዋታውን መርቼ ተመልሻለሁ፤ ስለጨዋታውም ያለኝን ሪፖርት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለሚመለከተው አካል አስገብቻለሁ፤ ሆኖም በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች ጣልቃ ገብነት እንዳለ ተድርጎ እየተዘገበ ያለው ነገር ከእውነት የራቀ መሆኑን ለመግለጽ እፈልጋለሁ፤ እንደዚህ ዓይነት ዘገባዎች ትክክል አይደሉም። የትኛውም የስራ አስፈጻሚ አካልም ሆነ ክለብ በእኔ ሪፖርታ ጣልቃ አልገባም። ” በሶሻል ሚዲያ የሃሰት ዘገባን እየጻፉ የሚገኙት አካላት ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያሳስባል።

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here